የምሥራቅ ሐረርጌ ዋሻዎች፤ የሳይንሳዊ ጥናትና የቱሪዝም አዲስ ተስፋ

You are currently viewing የምሥራቅ ሐረርጌ ዋሻዎች፤ የሳይንሳዊ ጥናትና የቱሪዝም አዲስ ተስፋ

AMN – መጋቢት 1/2018 ዓ.ም

በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የሚገኙና ለረጅም ዓመታት ሳይነኩ የቆዩ የተፈጥሮና የታሪክ ሀብቶችን እንዲሁም ዋሻዎች እምቅ የቱሪስት መስህቦችና የማዕድን ሀብቶች በባለሙያዎች ጥልቅ ጥናት ተደርጎባቸው ወደ ልማት ሊቀየሩ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የሚገኙና ለረጅም ዓመታት ሳይነኩ የቆዩ የተፈጥሮና የታሪክ ሀብቶች፣ በተለይም ዋሻዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በዞኑ የሚገኙ በርካታ ጥንታዊ ዋሻዎችንና የተፈጥሮ መስህቦችን በአካል ተዘዋውረው በተመለከቱበት ወቅት፣ ወደ 500 ሜትር ጥልቀትና 30 ሜትር ርዝመት ያለው አንድ ዋሻ ውስጥ ባደረጉት ጉብኝት፣ ነጭ የእብነበረድ ዓይነት፣ የኖራ ድንጋይና ግራናይት የሚመስሉ የተለያዩ ውድ ማዕድናት ድብልቅ ያላቸውን የከበሩ ድንጋዮች መመልከታቸውን ገልጸዋል።

እነዚህ ታሪካዊ ስፍራዎች ያላቸውን አመጣጥና የሰዎችን ሚና በትክክል ለመለየት በሙያተኞች ዕውቀትና በጠራ መረጃ ላይ የተመሠረተ ሰፊ ጥናት እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ምሥራቅ ሐረርጌ በዱር ፈረሶች፣ ዝሆኖች፣ ፍል ውኃዎች እንዲሁም እንደ ማርብልና ግራናይት ባሉ ውድ እና የከበሩ ድንጋዮች የበለጸገች መሆኑን አንስተዋል።

የሶማሌና የሐረሪ ክልሎችን ጨምሮ ቀጣናው መሠረተ ልማት ቢሟላለት በከፍተኛ ደረጃ ወደ ልማትና ሀብት ሊቀየር የሚችል እምቅ አቅም እንዳለውም አስረድተዋል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review