የሁለት ባለ 9 ወለል (G+8) ሕንፃዎች ግንባታ ለማስጀመር የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የሁለት ባለ 9 ወለል (G+8) ሕንፃዎች ግንባታ ለማስጀመር የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – መጋቢት 02/2018 ዓ.ም

ደሳሳ ቤቶችን በማንሳት የሁለት ተጨማሪ ባለ 9 ወለል (G+8) ሕንፃዎች ግንባታ ለማስጀመር የመሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥራ ማከናወናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

አምስት ነባር ቤቶችን በማንሳት በምትካቸው የተገነባውን ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት ቀድመው በቦታው ይኖሩ ለነበሩት ብቻ ሳይሆን፣ በአጠቃላይ በአካባቢው በደሳሳ የቀበሌ ቤቶች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ ለነበሩ ወገኖችም ጭምር መሆኑን ከንቲባዋ ገልጸዋል።

ዛሬ የመሠረት ድንጋይ በተጣለበት ቦታ ላይ ይኖሩ የነበሩት ወገኖች በዛሬው ዕለት ከንቲባዋ ባስረከቡት ባለ አራት ወለል ሕንጻ ውስጥ በመግባታቸው ደሳሳ ቤቶቹን በማንሳት ሁለት ተጨማሪ ባለ9 ወለል (G+8) ሕንፃዎችን ግንባታ ለማስጀመር የመሠረት ድንጋይ ሊቀመጥ መቻሉን ነው ያስታወቁት።

ቤት የማስተላለፊያ ሥነ ስርዓቱንም በመሠረታዊ ሪፎርም ሣራና አሠራሩን ግልጽ በማድረግ፣ በሕዝብ ፊት ዕጣ አውጥተን ቁልፍ በመስጠት የቤት ማስተላለፍ አሠራር ላይ ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል ።

የግንባታ ወጪውን በመሸፈን አብረውን በትብብር ለመገንባት ቃል ለገቡልን አዋሽ ባንክ እና ኤም ኤን አር ሲ (MNRC) ጥሬ ዕቃዎች አስመጪ እና ላኪ ድርጅት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ በማለት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review