ባለስልጣኑ ወንዝና የወንዝ ዳርቻ በመበከል ጉዳት ያደረሰው ዲሊዮ ፖል ኢንተርናሽናል ሆቴል መጸዳጃ ክፍሎቹን ማሸጉን አስታወቀ

AMN – መጋቢት 2/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት የሽንት ቤት ፍሳሽ ቆሻሻን በተደጋጋሚ ወደ ወንዝና የወንዝ ዳርቻ የለቀቀው ዲሊዮ ፖል ኢንተርናሽናል ሆቴል ለብክለቱ መነሻ ችግሩ የሆኑ ክፍሎቹን በማሸግ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ድርጊቱ የተፈጸመዉ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ባንቢስ አከባቢ ሲሆን ተቋሙ ከአሁን በፊት የሽንትቤት ፍሳሽን ወደ ወንዝ በመልቀቅ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመሆን የገንዘብ ቅጣት ጥሎበት ነበር።

መጀመሪያ ሆቴሉ ከጥፋቱ እንዲማር 300 ሺህ ብር ቅጣት ጥሎበት ከቅጣፋቱ ሳይማር በመቅረቱ በድጋሚ የቅጣቱን እጥፍ 600 ሺህ ተቀጥቶ ነበር። አሁንም ግን ድርጊቱን ለ3ኛ ጊዜ ባለማስተካከሉ ሆቴሉ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ የመጸዳጃ ክፍሎቹን እንዲታሸግ ተደርጓል።

ተቋሙን በቀጣይ በሕግ ተጠያቂ በማድረግ ላደረሰው ከፍተኛ ጉዳት በሕጉ መሠረት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።

በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶባቸው የተሰሩ ወንዝና የወንዝ ዳርቻዎች ልማቶች በመበከል ለታለመለት ዓላማ እንዳይውል በሚያደርጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ የሚወስደውን አስተዳደራዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ባለሥልጣኑ ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ ገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review