AMN – መጋቢት 2/2018 ዓ.ም.
የዕምነት ተቋማት ለኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥት ግንባታና ለሀገራዊ አንድነት ያበረከቱት አስተዋጽዖ ታላቅ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ዋና ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናገሩ።
ምክትል ከንቲባው ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ “የመደመር መንግሥት ለሃይማኖት ተቋማት ያለው ዕይታ” በሚል መሪ ሀሳብ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ ነው።

ምክትል ከንቲባው እንዳሉት የዕምነት ተቋማት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለሀገር ግንባታና ለሕዝቦች አብሮነት መጽናት መሠረት በመሆናቸው ተቋማቱ ከመንግሥት ጎን በመቆም ይህንን በጎ ሚናቸውን አጠናክረው ሊያስቀጥሉ ይገባል።
በመድረኩ ላይ የክፍለ ከተማው የእስልምና እምነት ተከታዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በቶማስ አሊጋዝ