የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ በጋሞ ዞና አርባ ምንጭ ከተማና አካባቢው የጣለው ከባድ ዝናብ ያደረሰውን ጉዳት በስፍራው በመገኘት ተመልክተዋል

You are currently viewing የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ በጋሞ ዞና አርባ ምንጭ ከተማና አካባቢው የጣለው ከባድ ዝናብ ያደረሰውን ጉዳት በስፍራው በመገኘት ተመልክተዋል

AMN መጋቢት 3/2018

በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖችና ለደረሰው የሃብት ውድመትም ሀዘናቸውን ገልፀው ለተጎጂ ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል።

አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማና አካባቢው በጣለው ከባድ ዝናብ የኩልፎ ወንዝ ሙላት ያስከተለውን ጉዳት በስፍራው ተገኝተው ተመልክተዋል።

በአደጋው በመንግሥትና የግል ተቋማት እንዲሁም መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት መድረሱን አንስተው፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን አፅናንተዋል።

የክልሉ መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ ለተጎጂዎች እየሰጡት ያለው እገዛና ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን አንስተው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።

በቀጣይነትም መንግሥት ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተጠናከረ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን መናገራቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review