ብልጽግናችን የሚረጋገጠው በዳበሩ ማህበራዊ እሴቶቻችንም ጭምር ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing ብልጽግናችን የሚረጋገጠው በዳበሩ ማህበራዊ እሴቶቻችንም ጭምር ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN መጋቢት 3/2018

እንደ ኢፍጣር ያሉ የዳበሩ ማህበራዊ እሴቶች ብልጽግናን ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና እንዳላቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) አዘጋጅነት በተከናወነው የኢፍጣር መርሐ ግብር ላይ ተገኝተዋል።

የኢፍጣር መርሐ ግብሩ ላይ ከከፍተኛ አመራሮች፣ የኢንቨስትመንት አጋሮችና የእምነቱ ተከታዮች ጋር በአንድነት የተደረገ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል። በእስልምና አስተምህሮ አብሮ መብላትና መረዳዳት ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው እሴት ነው ብለዋል።

“ጎረቤቱ ርቦት እርሱ ጠግቦ የሚያድር ከኛ አይደለም” የሚለው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምህሮ፣ ለሰው ልጅ ክብር መስጠትን፣ ርኅራኄን፣ የጋራ ደስታንና አብሮነትን በተግባር መተርጎም እንዳለብን የሚያሳይ ሕያው የሕይወት ስንቅ መሆኑን ተናግረዋል።

የዛሬው የኢፍጣር መርሐ ግብር የኢትዮጵያን የብዝኃነት ውበትና አብሮነትና አንድነት የሚያንጸባርቅ መሆኑንም ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በኢኮኖሚው ዘርፍ የምናስመዘግበው ስኬት ትርጉም የሚኖረው፣ ልክ እንደዛሬው የኢፍጣር መርኃ ግብር በታላቅ የፍቅርና የመተሳሰብ ሰንሰለት ተሳስረን ለትውልድ የምትተርፍ ጠንካራ ሀገርን በጋራ መገንባት ስንችል ነው ሲሉም ተናግረዋል። ብልጽግናችን የሚረጋገጠው እንዲህ ባሉ የዳበሩ ማህበራዊ እሴቶቻችን ጭምር ነው ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሁሉም የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የረመዳን እና የኢባዳ ጊዜ እንዲሆን ተመኝተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review