ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን ከ9 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል

You are currently viewing ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን ከ9 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል

AMN መጋቢት 4/2018

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን ድረስ ከ9 ሚሊዮን 36 ሺህ በላይ መራጮች መመዝገባቸውን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ማምሻዉን ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሀይሉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ቦርዱ የመራጮች ምዝገባን ለማድረግ ከቁሳቁስ ስርጭት ጀምሮ የሰው ሃይል የማሰልጠን እና መሰል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አድርጎ ወደ ስራ ገብቷል ብለዋል፡፡

ቦርዱ ከ52 ሺ 152 በላይ የምርጫ ጣቢያዎችን አቋቁሞ ወደ ትግበራ ገብቷል ያሉት ሰብሳቢዋ ከነዚህ የምርጫ ጣቢያዎች መካከል 6 ሺ 300 የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሳቢያ ወደ ስራ አለመግባታቸውንም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከመራጮች ምዝገባ ባለፈ የእጩዎች ምዝገባ ማከናወኑን ገልጸው የፓርቲዎች የክርክር መድረክ፣ የፓርቲዎች የገንዘብ ድጋፍ፣ የነፃ የአየር ሰዓት እና መሰል ስራዎች በአግባቡ መሰራታቸውንም አስታውቀዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review