AMM – መጋቢት 5/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተሰጠውን ህግን የማስከበር ተልዕኮ በውጤት ከማከናወን ባለፈ ራሱን በስፖርት በማዳበር ሃገር አቀፍና የከተማ ተልእኮዎችን በአገባቡ መወጣቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ ተናገሩ፡፡
2ኛው ከተማ አቀፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ የስፖርት ውድድር ተካሂዷል፡፡
ፖሊስ የተሰጠውን ህግን የማስከበር ተልዕኮ በውጤት በማከናወን ላይ ይገኛል ያሉት የአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ፣ ሃገር አቀፍና የከተማ ተልእኮዎችን በአገባቡ መወጣቱን አጠናክሮ እንዲመቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
በቀጣይም ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እዲንጠናቀቅ ሙሉ ዝግጅት ማድረጉን ዋና አዛዙ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ልማት ያለ ፖሊስ ተሳትፎ አይረጋገጥም፤ ለዚህም ለፖሊስ አስተዋጽኦ ምስጋና ያቀረቡት የእለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ በቀጣይም ራሱን በስፖርት ያዳበር ፖሊስ በመገንባትና ሰላምን በማረጋገጥ እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
የፖሊስ ስፖርት ፌስቲቫል ውድድሩ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ፖሊስ መምሪያዎች፣ ማዕከላትና በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ፣ በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ውድድሩ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ከፖሊስ ጣቢያ ጀምሮ የማጣሪያ ውድድሮችን አልፈው የመጡ ተወዳዳሪ ስፖርተኞች ተሳታፊ የሆነበት ነው፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ኮሚሽነሮች፣ የአዲስ አበባ ስፖርት ቢሮ ሃላፊዎች እንዲሁም ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የፖሊስ አባላት ታድመዋል፡፡
በአንዋር አህመድ