የኦሮሞ ህዝብ ጥቅም የሚረጋገጠው በውይይት እንጂ በአፈሙዝ አይደለም — አቶ ከፍ ያለው ተፈራ

You are currently viewing የኦሮሞ ህዝብ ጥቅም የሚረጋገጠው በውይይት እንጂ በአፈሙዝ አይደለም — አቶ ከፍ ያለው ተፈራ

AMM – መጋቢት 5/2018 ዓ.ም

“በወንድማማቾች መካከል የመሳሪያ ድምጽ ይቁም፣ ዘላቂ ሰላም ይስፈን” በሚል መሪ ሀሳብ በኦሮሚያ ክልል የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

ውይይቱን የከፈቱት በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከፍ ያለው ተፈራ፣ የኦሮሞ ህዝብ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችሉ የዳበሩ ባህላዊ እሴቶች እንዳሉት ገልጸዋል። `

አቶ ከፋያለው አክለውም በክልሉ የሚስተዋሉ የሀሳብ ልዩነቶች በአፈሙዝ ሳይሆን በውይይት መፈታት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በአፈሙዝ የሚመለስ ጥያቄ እንደሌለና የኦሮሞ ህዝብ የሚፈልገው ሰላምና ልማት ብቻ መሆኑን ተገልጿል።

በክልሉ የሚደረጉ አላስፈላጊ ግጭቶች ተጠቃሚው ህዝቡ ሳይሆን የኢትዮጵያ ጠላቶች መሆናቸውን አቶ ከፍ ያለው አስገንዝበዋል።

በተለይም ወጣቱ የሰላም ዘብና ችግር ፈቺ በመሆን ከልማት ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።

የጥይት ድምጽ የማይሰማባት ኦሮሚያን እውን በማድረግ፣ የኦሮሞ ህዝብ በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ያለውን ተሳትፎ እንዲያጠናክር ጥሪ ተላልፏል።

በመድረኩ ላይ ከክልሉ የተወጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በሔኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review