የወሎ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደርበትን የምርጫ ማኔፌስቶ ይፋ አደረገ

You are currently viewing የወሎ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደርበትን የምርጫ ማኔፌስቶ ይፋ አደረገ

AMM – መጋቢት 5/2018 ዓ.ም

የወሎ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደርበትን የምርጫ ምልክት እና የምርጫ ማኔፌስቶ የማስተዋወቂያ መርሃ ግብረ እያካሄደ ነው።

ፓርቲው ‘ከውሃ እስከ ውሃ ” በሚል መሪ ሀሳብ ባካሄደው መርሃ ግብር የፓርቲው የምርጫ ምልክት “ቁልፍ ” መሆኑ ይፋ አድርጓል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የወሎ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት ነጻነት ጣሰው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ምልክቱም የኢትዮጵያን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች መፈቻ ነው ብለዋል።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እደተሳካ ሁሉ የባህር በር ጥያቄን ለማሳካት መክፈቻ ቁልፍን ለፓርቲያችን ምልክት አድርግና ብለዋል።

ፓርቲው በኢኮኖሚያዊ፣ በፖለቲካዊ እና በማህበራዊ ፕሮግራሞቹን ላይ ያተኮረውን የምርጫ ማኒፌስቶውን ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያን ጉደለቶች አሟልተን የኢትዮጵያን ትንሳኤ እናበስራለን ያሉት ፕሬዚዳንቱ ከጋምቤላ እና ከትግራይ ውጭ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች እንደሚወዳደሩም ገልጸዋል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review