AMN መጋቢት 5/2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጉብኝት ተመልሰው በቀጥታ ወደ አርባምንጭ አቅንተዋል።
በአርባ ምንጭ ዙሪያ እና በመላው ጋሞ ዞን በደረሰው አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ሐዘናቸውን ለመግለጽ እና የሚከናወኑ የድጋፍ ስራዎችን ይገመግማሉ።
ለቀናት የዘለቀው ከባድ ዝናብን ተከትሎ በአካባቢው የተከሰተው ጎርፍ፤ የመሬት መንሸራተት አደጋ የዜጎቻችንን ህይወት ቀጥፏል፣ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል። ከመጠን በላይ የሞላው የኩልፎ ወንዝም መንደሮችን፣ ቤቶችን፣ የእርሻ ስፍራዎችን፣ የአካባቢ መሠረተ ልማትን አውድሟል።
ማኅበረሰቡ በከባድ ሀዘን በሚገኝበት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የነፍስ አድን ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ከተጎጂ ቤተሰቦች ጎን መቆም ይገባናል። -የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት