AMN-መጋቢት 05/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያን ሄራልድ (The Ethiopian Herald) ጋዜጣ በየካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትሙ የአዲስ አበባን አስደናቂ ለውጥ በተመለከተ ሰፊ የዘገባ ሽፋን ሰጥቷል።
ጋዜጣው “አዲስ አሰንዲንግ” (Addis Ascending) በተሰኘው እና በሰለሞን ኃይሉ በተፃው አምድ የአዲስ አበባን ፈጣን ለውጥ እና የኮሪደር ልማት ስኬቶችን በሚከተለው መልኩ ዳስሶታል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
የከተማ እድሳትና የኮሪደር ልማት፦ የወንዞች ዳርቻ ልማት ከውበት ባለፈ፣ ዘመናዊ መንገዶችን፣ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገዶችን እንዲሁም መናፈሻዎችን በማካተት የከተማዋን ነዋሪ ህይወት እየቀየረ ይገኛል።

የሀገር በቀል እውቀትና ዘመናዊነት ጥምረት፦ ግንባታው የዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና የሀገር በቀል እውቀት (ለምሳሌ የኮንሶ የእርከን ስራ ጥበብ) ውጤት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።
አዲስ የስራ ባህል፦ ፕሮጀክቱ በ24/7 የስራ ባህል እና በቁርጠኝነት “አይቻልም” የሚለውን መንፈስ በመስበር፣ ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ትልልቅ ስራዎችን የመስራት ብቃቷን ያሳየችበት ነው።
ደህንነትና ጤና፦ ቀደም ሲል ለጎርፍ እና ለበሽታ ተጋላጭ የነበሩ አካባቢዎች ዛሬ ወደ ጽዱ፣ አረንጓዴ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ ማራኪ ስፍራዎች ተቀይረዋል።
አዲስ አበባ ዛሬ በዲፕሎማሲ ብቻ ሳይሆን በዘመናዊ ከተማ ግንባታም ለአፍሪካ አዲስ ተስፋ እየሆነች ነው!