በኪነ-ጥበብ ዘርፎች ተተኪ ባለሙያዎችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ነው

You are currently viewing በኪነ-ጥበብ ዘርፎች ተተኪ ባለሙያዎችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ነው

AMM – መጋቢት 5/2018 ዓ.ም

በኪነ-ጥበብ ዘርፎች ተተኪ ባለሙያዎችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ የባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ገለፅ፡፡

“የጥበብ ስጦታ ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚህ 17ኛው የኪነ-ጥበብ ፌስቲቫል ሳምንት በመስቀል አደባባይ ተከፍቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ሀላፊ ኂሩት ካሳው (ዶ/ር) ኪነ-ጥበብ ማንነትን በመቅረፅ ታሪክን በማስረፅ ረገድ ሚናው ከፈተኛ መሆኑን አንስተው፣ በየአመቱ የሚከናወነው የኪነ-ጥበብ ፌስቲቫል በኪነ-ጥበብ ዘርፎች ተሰጥዖ ያላቸውን ወጣቶች ወደፊት በማምጣት ተተኪ ባለሙያዎችን ለማፍራት ያለመ ነው ብለዋል፡፡

አዲስ አበባን በጥበብ ለመሸመን ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ያነሱት የቢሮ ሀላፊዋ ለዚህም የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ የተሰሩ ሲኒማዎችና አንፊ ትያትሮች ህያው ምስክር ናቸው ብለዋል፡፡

ሀላፊዋ አክለውም ኪነ-ጥበበ በትውልድ መካከል የባህል ትስስር ለመፍጠር ህብረ ብሔራዊነት፣ አንድነትና አብሮነት ለማጉላት እንዲሁም የጋራ ትርክትን ለመገባት ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን አስተውሉ፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ይህንን መሳሪያ ለሀገረ መንግስት ግንባታ ሊጠቀሙበት እንደሚገባም መልዕልት አስተላልፈዋል፡፡

በፌስቲቫሉ መክፈቻ ላይ ባህላዊና ዘመናዊ ውዝዋዜ፣ ሰርከስና ሌሎች የኪነ-ጥበብ ስራዎች ቀርበዋል፡፡

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review