ማንችስተር ሲቲ ከዋንጫ ፉክክሩ ያራቀውን ውጤት አስመዘገበ

You are currently viewing ማንችስተር ሲቲ ከዋንጫ ፉክክሩ ያራቀውን ውጤት አስመዘገበ

AMN-መጋቢት 5/2018 ዓ.ም

በ30ኛ ሳምንት የሊግ መርሐግብሩ ዌስትሃም ዩናይትድን የገጠመው ማንችስተር ሲቲ ከዋንጫ ፉክክር ያራቀውን የአቻ ውጤት አስመዝግቧል።

በለንደን ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ 1ለ1 ሲጠናቀቅ ሲቲ በርናርዶ ሲልቫ ባስቆጠረው ግብ መምራት ችሎ ነበር።

ዌስትሃም ዩናይትድ ግን በቀድሞ የአርሰናል ተከላካይ ኮኒስታንቲኖስ ማቭሮፓኖስ ግብ አቻ ሆኗል።

አንድ ቀሪ ጨዋታ ያለው ማንችስተር ሲቲ ከመሪው አርሰናል ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ዘጠኝ ሆኗል።

የዛሬውን ጨዋታ በቅጣት ያልመራው ፔፕ ጋርዲዮላ ከጨዋታው በፊት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ነጥብ ከጣልን የዋንጫው ፉክክር ያበቃል ብሎ ነበር።

በሂሳባዊ ስሌት ብዙ ነገር መቀያየር ቢችልም ማንችስተር ሲቲ እያሳየ ካለው አቋም መነሻ አርሰናል ከ22 ዓመት በኋላ የሊግ ዋንጫ የማሸነፍ እድሉ የሰፋ መስሏል።

ዌስትሃም ዛሬ ባገኘው ውጤት ነጥቡን 29 በማድረስ ለጊዜው ከወራጅ ቀጠናው ወጥቷል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review