AMN-መጋቢት 5/2018 ዓ.ም
አርሰናል በ30ኛ ሳምንት የሊግ መርሐግብሩ ከኤቨርተን ጋር ተጫውቶ 2ለ0 አሸንፏል።
በኤቨርተን የተፈተኑት መድፈኞቹ ተቀይሮ በገባው አጥቂው ቪክቶር ዮኬሬሽ እና ማክስ ዶውማን ግቦች ወሳኝ ሦስት ነጥብ አሳክተዋል።
ተቀይሮ ከገባ በኋላ ልዩነት የፈጠረው የ16 ዓመቱ ማክስ ዶውማን በፕሪምየር ሊጉ ግብ ያስቆጠረ በእድሜ ትንሹ ተጫዋች ሆኗል።
ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን ልዩነት ወደ 10 ነጥብ አስፍቷል።
ነገር ግን ሲቲ ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር የሚያደርገውን ጨምሮ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች ይቀሩታል።
በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ሌላ ጨዋታ ኒውካስትል ዩናይትድ ቼልሲን 1ለ0 አሸንፏል።
በስታምፎርድብሪጅ በተደረገው ጨዋታ አንቶኒ ጎርደን የኒውካስትልን ግብ አስቆጥሯል።
በሸዋንግዛው ግርማ