AMN መጋቢት 5/ 2018 ዓ/ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከፋሲካ ኪነ ጥበብ እና ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር ” አንድ ልብ አንድ ምት ” በሚል መሪ ቃል በአድዋ ድል ፕላዛ ከ10ሺ በላይ ወጣቶች የተሰታፉበት ደማቅ የኪነ ጥበብ ትዕይንት አካሄዷል።
የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ክብረ-ዓለም ደምሴ መድረኩ ወጣቶችን ለማነቃቃት እና ለላቀ ስራ ለማበረታት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
ዳንስን በተለያዩ ቅርጽ በማቀናጀት የተካሄደው ትዕይነት፣ ጤናማና ንቁ ትውልድ ለመገንባት ያስችላል፡፡
እንዲህ ያሉ ማራኪ መድረኮች በኮሪደር ልማት በተዋቡ ቦታዎች መካሄዱ ወጣቶች ችሎታቸውን ለበጎ ተግባር እንዲያውሉ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።
በአድዋ ድል ፕላዛ በተዘጋጀው የአደባባይ ኪነ ጥበብ ትዕይንት ላይ በዘመናዊ ዳንስ እና በባህላዊ ውዝዋዜ የታጀበ አሰደሳች የጥበብ መድረክ ላይ ታዋቂ አርቲስቶች፣ ቲክቶከሮች እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች መገኘታቸዉን ቢሮዉ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል።