“የሃይማኖት ተቋማት በመደመር መንግስት እይታ” በሚል መሪ ሀሳብ፣ በከተማችን ከሚገኙ የእስልምና እምነት አባቶች እና ምእመናን ጋር ዛሬ ማለዳ ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል።

ኢትዮጵያ የብዝሃ ሃይማኖት፣ ባህል እና ቱፊት ባለቤት የሆነች ሀገር ናት። አንዱ ደምቆ ሌላው ደብዝዞ የሚታይባት ሳትሆን፣ ሁሉም ሃይማኖቶች በእኩልነት የሚደምቁባት ናት። እንደ መንግስትም ሁሉንም ሃይማኖቶች በእኩልነት እንመለከታለን፤ በእኩልነት እናገለግላለን።

እንደ ሌሎቹ ሀይማኖቶች ሁሉ፤ እስልምና የኢትዮጵያን ጥንታዊ ቅርሶች፣ ታሪኮችና ቱፊቶች ጠብቆ ለትውልድ በማሸጋገር፣ ብሄራዊ ጥቅምን በማስጠበቅ፣ ግብረ-ገብነትንና ሰብአዊ ርህራሄን በማስተማር፣ እንዲሁም በልማት ተሳትፎው የዛሬዋን ኢትዮጵያ በመገንባት ረገድ ያለው ሚና የጎላ ነው።

በታሪክ ብቻ ሳሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት የሃይማኖት ተቋማት በከተማችን ሁለንተናዊ የሰላም ግንባታ፣ የልማት እና የብልፅግና ጉዞ ላይ እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ የማይተካ ነው።

በውይይታችንም ይህንን ጉልህ ሚና ይበልጥ በማጠናከር እጅ ለእጅ ተያይዘን ለልማት፣ ለህዝቦች ትስስር መጎልበት፣ ለሰላም እና የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በጋራ የምንቆምበት እና በጋራ የምንሰራበት አግባብ ላይ ተግባብተናል።

እንዲሁም የውይይት መድረኩ በሂደት የታዩ ክፍተቶችን ማረም በሚቻልበት አግባብ ላይ በመወያየት በትብብር ለማረም የሚስችል መደላድል የፈጠረ ውጤታማ መድረክ ነበር።

ይህ መድረክ በየክፍለ ከተማው ሲካሄዱ የቆዩ ውይይቶች ማጠቃለያ ሲሆን፣ የመንግስትንና የሃይማኖት ተቋማትን ሚና እና ድርሻ በግልጽ ለይቶ ያስቀመጠ እንዲሁም የጋራ መግባባት የተፈጠረበት ነው።

ክቡራን የከተማችን የእስልምና እምነት አባቶች እና ምዕመናን፤ ለነበራችሁ ከፍተኛ ተሳትፎ፣ ለሰጣችሁን ገንቢ ሐሳብና አስተያየት በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።

ረመዳን ሙባረክ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንታባ አዳነች አቤቤ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review