በከተማዋ የታየው ፈጣን ለውጥና የልማት ተነሳሽነት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ትልቅ ምሳሌ ነዉ – የሚዲያ ባለሙያዎች

You are currently viewing በከተማዋ የታየው ፈጣን ለውጥና የልማት ተነሳሽነት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ትልቅ ምሳሌ ነዉ – የሚዲያ ባለሙያዎች

AMN መጋቢት 06/ 2018 ዓ.ም

በከተማዋ የታየው ፈጣን ለውጥና የልማት ተነሳሽነት ለሌሎችም የአፍሪካ ሀገሮች ምሳሌ የሚሆን መሆኑን የሚዲያ ባለሙያዎች ገለጹ።

ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች በከተማዋ እየተሰሩ የሚገኙ የቱሪዝም መሰረተ ልማቶችና ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

አዲስ አበባ ለአፍሪካውያን እና በቀሪው ክፍለ ዓለማት ላሉ ጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነችው ከተማ ላይ የታየው ፈጣን ለውጥና የልማት ተነሳሽነት ለአፍሪካውያን ምሳሌ እንደሚሆን ተናግረዋል።

ጋዜጠኞቹ መዲናዋ ያላትን ገናና ታሪክ እና የተጣለባትን ታሪካዊ ኃላፊነት በዘላቂነት እየተወጣች መሆኗን ገልፀው ያዩትን ተጨባጭ የከተማዋን ሁለንተናዊ ፈጣን እድገት ለሌሎች በማጋራት የሙያ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review