AMN- መጋቢት 07 /2018 ዓ/ም
ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት መሳለሚያ አካባቢ ከሚገኝ አንድ የነዳጅ ማደያ ሲሆን በማደያው በነዳጅ መቅዳት ሙያ ላይ የተሠማራው አሸናፊ ጥላሁን እና ሱልጣን ተክላይ የተባለ አሽከርካሪ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
ግለሠቦቹ ጨለማን ተገን በማድረግ ከተጠቀሰው የነዳጅ ማደያ የቀዱትን 6 በርሜል ወይም 1200 ሊትር ነዳጅ ኮድ 3 A 55857 አ/አ FSR ተሽከርካሪን በመጠቀም ጭነው ሲያዘዋውሩ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ፔፕሲ አካባቢ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስረድቷል።
ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ባደረገው ምርመራም ነዳጁን በህገ ወጥ መንገድ ከከተማው ክልል ለማስወጣት ሲንቀሳቀሱ እንደነበርም ገልጿል።

ወቅታዊውን ዓለማቀፉዊ ሁኔታ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጥቶበት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባን የነዳጅ ምርት በህገ ወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩ፣ ነዳጅ የሚደብቁና መሠል የወንጀል ድርጊት ውስጥ በሚገቡ የነዳጅ ማደያዎች፣ ሠራተኞችና ግለሠቦች ላይ የሚወስደውን ህጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።