AMN-መጋቢት 7/2018 ዓ.ም
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 30ኛ ሳምንት መርሐግብር የመጨረሻ ጨዋታ ያከናወኑት ብሬንትፎርድ እና ዎልቭስ 2ለ2 ተለያይተዋል።
በጌትች ኮሚኒቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ባለሜዳው ብሬንትፎርድ ማይክል ካዮዴ እና ኢጎር ቲያጎ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2ለ0 የመምራት ዕድል አግኝቶ ነበር።
በሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች አስቶንቪላ እና ሊቨርፑልን ያሸነፈው ዎልቭስ በቀላሉ እጅ ሳይሰጥ አዳም አርመስትሮንግ እና ቶሉ አሮኮዳሬ ከመረብ ባሳረፏቸው ኳሶች ነጥብ ተጋርቷል።
በርካቶች ከጠበቁት በላይ ጥሩ የውድድር ዓመት እያሳለፈ የሚገኘው ብሬንትፎርድ በ45 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በቅርብ ሳምንታት ብቃቱን ያሻሻለው ዎልቭስ በአንፃሩ በ17 ነጥብ የደረጃውን ግርጌ ይዟል።
በሸዋንግዛው ግርማ