AMN – መጋቢት 8/2018 ዓ.ም
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በከተማ ልማት ፖሊሲ ዙሪያ ኤኤምኤን ፕላስ ባዘጋጀው የክርክር ማድረክ ላይ የሃሳብ ፍልሚያ አድርገዋል።
በክርክሩ ላይ
1. የአዲሱ ትውልድ ፓርቲ
2. የኢትዮጵያ አንድነት ጥምረት ፓርቲ
3. የብልጽግና ፓርቲ እና
4. የወሎ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ተሳትፈዋል፡፡
እነዚህ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሰጣቸው መድረክ ላይ የቀረጹትን የከተማ ልማት ፖሊሲ እና ከተሞችን የሚያስተዳድሩበትን ማኒፌስቶ ለሚመርጣቸው ሕዝብ አቅርበዋል።
ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ በከተማ ልማት የዜጎችን ሕይወት እንዴት እንደሚለውጡ ያላቸውን የሃሳብ አማራጭ አንጸባርቀዋል።

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ቢመረጡ በፍጥነት እየጨመረ የመጣውን የከተማ ነዋሪ ቁጥር እንዴት እንደሚመሩ እና የነዋሪዎችን ፍላጎት የሚያሟሉበትን መንገድም በመድረኩ አብራርተዋል።
በተጨማሪም ፓርቲዎቹ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 4 ላይ የሰፈረውን የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ ሊያገኝ ስለሚገባው ልዩ ጥቅም በተመለከተ ያላቸውን የፓርቲ አቋምም ገልጸዋል።
ይህ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ክርክር ሐሙስ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ በኤኤምኤን ፕላስ ላይ ይተላለፋል።
በወርቅነህ አቢዮ