ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኮሪደር ልማት የተገነቡ 315 የንግድ ሱቆችን፣ በቀበሌና በንግድ ቤቶች በኪራይ ሲሰሩ ለነበሩ የኮሪደር ልማት ተነሺዎች በዕጣ አስተላለፉ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኮሪደር ልማት የተገነቡ 315 የንግድ ሱቆችን፣ በቀበሌና በንግድ ቤቶች በኪራይ ሲሰሩ ለነበሩ የኮሪደር ልማት ተነሺዎች በዕጣ አስተላለፉ

AMN መጋቢት 8/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ በኮሪደር ልማት የተገነቡ 315 የንግድ ሱቆችን፣ በቀበሌና በንግድ ቤቶች በኪራይ ሲሰሩ ለነበሩ የኮሪደር ልማት ተነሺዎች በዕጣ አስተላልፈናል ብለዋል፡፡

በከተማችን ከዚህ ቀደም የመንግስት የቀበሌና የንግድ ቤቶችን ተከራይተው ሲሰሩ ለነበሩ ነዋሪዎች አስተዳደራችን ሁለት አማራጮችን አቅርቦ እንደየምርጫቸው በአክሲዮን ተደራጅተው ወደ ንግድ ሱቃቸው ገብተው ሥራ እንዲጀምሩ፣ ይህ ካልሆነም መንግስት የሚያቀርብላቸውን ሱቆች ተከራይተው እንዲሰሩ እድል ሰጥቶ ነበር።

አብዛኛዎቹ መንግስት ገንብቶ ያቀረብላቸውን ሱቆች ተከራይተው ንግዳቸውን የቀጠሉ ሲሆን፣ በአክሲዮን ተደራጅተው ወደ ንግድ ሱቃቸው ገንብተው ለመነገድ የመረጡም በርካቶች ነበሩ። ከእነዚህ በአክሲዮን እንዲደራጁና መሬት ተረክበው እንዲገነቡ ከተፈቀደላቸው ውስጥ የመገንባት አቅም በማጣታቸው በተለያዩ የውይይት መድረኮች ሌላ አማራጭ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል ብለዋል፡፡

በመሆኑም አስተዳደራችን ችግሩን ለመቅረፍ፤ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ ዳርቻ ልማት እና በመልሶ ማልማት ሥራዎች ምክንያት ለተነሱ ነዋሪዎች፤ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች በኮሪደር ልማቱ የተገነቡ 315 ዘመናዊ የንግድ ሱቆችን በዕጣ እንዲተላለፉላቸው አድርጓል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review