AMN መጋቢት 8/2018 ዓ.ም
ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ከተሾሙት በኢትዮጵያ የጣሊያን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም አዲስ አበባ ከጣሊያን ከተሞች ጋር ያላትን ትብብር እና አጋርነት አጠናክሮ ለማስቀጠል፤ እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መካከል ያለውን የቆየ የታሪክ፣ የባህል እና የልማት ትብብር ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ምክክር አድርገዋል።
ኢትዮጵያና ጣሊያን የቆየ የታሪክ፣ የባህል፣ የልማት ትብብር እና የሁለትዮሽ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ያላቸው አገራት መሆናቸዉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡