የሃይማኖት መሪዎች ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን ጨምሮ በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ ሃይማኖታዊ ጽንፈኝነትን፤ አክራሪነትን እና አክቲቪዝምን ሊታገሉ ይገባል

You are currently viewing የሃይማኖት መሪዎች ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን ጨምሮ በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ ሃይማኖታዊ ጽንፈኝነትን፤ አክራሪነትን እና አክቲቪዝምን ሊታገሉ ይገባል

AMN መጋቢት 9/2018 ዓ.ም

የሃይማኖት መሪዎችፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን ጨምሮ በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ ሃይማኖታዊ ጽንፈኝነትን፤ አክራሪነትን እና አክቲቪዝምን ሊታገሉ እንደሚገባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “የሃይማኖት ተቋማት በመደመር መንግስት እይታ” በሚል መሪ ሀሳብ ከኢትዮጵያ ወንጌላውያን፣ ከካቶሊክ እና ከሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያናት መሪዎች ጋር ዉይይት አካሂዷል፡፡

ነዋሪዎቹን ያወያዩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሰጡት ምላሽ በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ ተገቢ ያልሆኑ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች በማህበረሰቡ ዉስጥ ጥል፤ ክርክር፤ ክፍፍልን እና ግጭትን ሊፈጥሩ እንደሚችሉ አስገንዝበዋል፡፡

ለአንደኛዉ ሃይማኖት የተቆረቆሩና ቀናኢ በመምሰል በሌላኛዉ ሃይማኖት ላይ የሚሰነዘሩ አስተያየቶች ፤ ሃሳቦች እና ሌሎች ተግባራትን

በጋራ መታገል ይገባል፡፡

የሃይማኖት ተቋማት የተመሰረቱበት ዋንኛ አላማ መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠት ነዉ ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሃይማኖታዊ መርህ ባፈነገጠ መንገድ መጓዝ ተቋምን ያዳክማል፤ ህዝብ እና ሃገርን ይጎዳል፡፡

በሃይማኖታዊ ተቋማት ዉስጥ ሥርዓት የሚጥሱ ጉልበተኞች በሚፈጠሩበት ወቅት ሃይማኖታዊ ተቋማት እየተዳከሙ፤ ጉልበተኞች እየፈረጠሙ እንደሚሄዱ ነዉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተናገሩት፡፡

ችግሮች በሚፈጠሩበት ወቅት ለአንደኛዉ ሃይማኖት ድምጽ ለመሆን በሚል ሽፋን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ መረጃዎች መፍትሄ እንደማያመጡ እና ይልቁንም በሃይማኖት ተቋማት እና በማህበረሰቡ ዉስጥ ቅራኔ እንደሚያስፋፉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የሃይማኖት ተቋማት እና መሪዎች ችግሮች ቢኖሩ እንኳ ተቋማዊ አሰራርን ተከትለዉ መፍታት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የሃይማኖታዊ ተቋማትን ህግ እና ሥርዓት ባላከበረ መንገድ ለሃይማኖት ድምጽ ለመሆን በሚል ሽፋን የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የቤተ እምነቱን አሰራር ከመጣስ እና የግጭት መንስኤ ከመሆን ባለፈ በሃገርና በህዝብ ላይ ጉዳት ስለሚያስከትሉ የሃይማኖት መሪዎች መሰል ድርጊቶችን በቁርጠኝነት ሊታገሉ ይገባል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review