የኢትዮጵያ እና ቻይና ልዑካን በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ላይ ሊኖሩ በሚችሉ የፋይናንስ አማራጮች ዙሪያ መከሩ

You are currently viewing የኢትዮጵያ እና ቻይና ልዑካን በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ላይ ሊኖሩ በሚችሉ የፋይናንስ አማራጮች ዙሪያ መከሩ

AMN መጋቢት 9/ 2018 ዓ.ም

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በኢትዮጵያ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ አምባሳደር ቼን ሃይ እና ከቻይና ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (China Exim Bank) ከመጡ የልዑካን ቡድን ጋር በጋራ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።

ውይይቱ በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ላይ ሊኖሩ የሚችሉ የፋይናንስ አማራጮችን በማፈላለግ ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በቡድን 20 (G20) የብድር ማዕቀፍ ስር እየተከናወነ ባለው የብድር ሽግሽግ ሂደት ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችን በተመለከተ መክረዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ ቻይና የብድር ሽግሽግ ሂደቱን በሚመራው ይፋዊ የአበዳሪዎች ኮሚቴ (OCC) ውስጥ በሊቀ-መንበርነት ላሳየችው አመራርና በሂደቱ ሁሉ ላደረገችው ገንቢ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የብድር ሽግሽግ ሂደቱ አሁን ላይ በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የጠቀሱት አቶ አህመድ፣ የተጀመረው መነቃቃት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

አያይዘውም ከንግድ አበዳሪዎች ጋር የሚደረገው ድርድር እንዲጠናቀቅ ቻይና የምታደርገውን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በበጎ እንደሚመለከቱት መግለጻቸዉን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አመላክቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review