AMN መጋቢት 10 / 2018 ዓ.ም
የ1447ኛው የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል የሶላት ሥነ-ሥርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
በበዓሉ ዕለት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የሚዘጉ መንገዶችን ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።
ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ ዋና ዋና መንገዶች፡-
ከመገናኛ፡ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጡ (ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ)።
ከቦሌ፡ በአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል የሚሄዱ (አትላስ መብራት እና ፒኮክ መብራት ላይ)።
ከወሎ ሠፈር፡ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ የሚመጡ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)።
ከአጎና መስቀለኛ፡ ወደ ጥላሁን አደባባይ የሚመጡ ከባድ ተሽከርካሪዎች (አጎና ሲኒማ ላይ) እና ቀላል ተሽከርካሪዎች (ጥላሁን አደባባይ ላይ)።
ከቡልጋሪያ መብራት፡ ወደ ገነት ሆቴልና ሜክሲኮ የሚሄዱ (ቡልጋሪያ መብራት ላይ)።
ከጦር ኃይሎች፡ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ሜክሲኮ የሚመጡ (ከፍተኛ ፍርድ ቤት አደባባይ ላይ)።
ከመገናኛ (ሲግናል)፡ በሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ የሚሄዱ (ሴቶች አደባባይ ላይ)።
ከአራት ኪሎ፡ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚሄዱ (4 ኪሎ አደባባይ ላይ)።
ከቴዎድሮስ አደባባይ፡ በቸርችል ጎዳና ወደ አገር አስተዳደር መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ)።
ከበዓሉ ዋዜማ ምሽት ጀምሮ በተጠቀሱት መንገዶች ላይ ተሽከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት አቁሞ መሄድ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ ገልጿል፡፡