በበዓላት የሚከናወን የበጎ አድራጎት ተግባር የመደጋገፍባህል እያደገ መምጣቱን አመላካች ነው ተባለ

You are currently viewing በበዓላት የሚከናወን የበጎ አድራጎት ተግባር የመደጋገፍባህል እያደገ መምጣቱን አመላካች ነው ተባለ

በዓላትን ምክንያት በማድረግ የሚከናወኑ የበጎ አድራጎት ተግባራት በመዲናዋ የመረዳዳት እና የመደጋገፍ ባህል እያደገ መምጣቱን አመላካች ስለመሆኑ ተገልጿል

1 ሺህ 447ኛውን የኢድ አል-ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ በከተማዋ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ 28ቱም የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት አቅመ ደካሞችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ አረጋውያን እና ለከፋ ማህበራዊ ችግር ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች ማዕድ የማቋደስ መርሃ ግብር ተከናውኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኘው 6ኛው እና በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በሚገኘው 21ኛው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት በመገኘት ማዕድ በማቋደስ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በወቅቱ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች፣ በመዲናዋ የመረዳዳት እና የመደጋገፍ ባህል እያደገ መሆኑን አንስተው፣ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተከናወነው የበጎ አድራጎት ተግባርም ይህንን የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀዋል።

ከንቲባ አዳነች አክለውም፣ “ያደረግንላችሁን ጥሪ በመቀበል በማዕከላቱ እየመገባችሁ ለምትገኙ ባለሀብቶች፣ አጋሮች እና አስተባባሪዎች በተጠቃሚዎቹ ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በዓሉ የደስታና አብሮነት የሚጎለብትበት ይሁንልን”  ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች በዓሉ የደስታና አብሮነት የሚጎለብትበት እንዲሆንም ተመኝተዋል።

ማዕከላቱ በዐቢይ ጾም እና በረመዳን ወቅትም ጭምር ለጾመኞች እንደየ እምነታቸው የአፍጥር እና የፆም ምገባ አገልግሎት ሲሰጡ መቆየታቸው ተጠቁሟል፡፡

በሳህሉ ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review