የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለኢድ አል-ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

You are currently viewing የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለኢድ አል-ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

AMN መጋቢት 11/2018

ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች እና አምባሳደሮች ለ1447ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ መስሊሞች በዓሉ ሰላም፣ ደስታ እና ብልጽግናን ይዞ እንዲመጣ ተመኝቷል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በሀገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም የኢድ አል-ፈጥር በዓልን ለሚያከብሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሙሉ መልካም ምኞቱን ገልጿል።

በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል- ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን የገለጸው በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ነው።

በኢትዮጵያ የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ በዓሉ የበጎነት፣ የብልጽግና እና የበረከት እንዲሆን ተመኝቷል።

በኢትዮጵያ የፓኪስታን ኤምባሲ በኢትዮጵያ እና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ሙስሊሞች በዓሉ የደስታና የበረከት እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል። በመላው ዓለም ለሚገኙ ሙስሊሞች በዓሉ የሰላም እና የብልጽግና እንዲሆን የተመኘው ደግሞ በኢትዮጵያ የአልጄሪያ ኤምባሲ ነው።

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል አደረሳችሁ ብሏል።

በኢትዮጵያ የጅቡቲ አምባሳደር አብዲ መሐሙድ አይቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኢድ አል-ፈጥር በዓል ለሁሉም ጤናን፣ ደስታን፣ ሰላምንና ብልጽግናን ይዞ እንዲመጣ እመኛለሁ ብለዋል።

በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ስቲያን ክሪስቲያንሰን ለእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የኢድ አል-ፈጥር በዓል እንዲሆን ተመኝተዋል።

ዩናይትድ ኪንግደም፣ ስዊድን፣ ስዊዘርላንድ፣ ጀርመን፣ አርሜኒያ፣ አውስትራሊያ እና ካናዳ እና ሌሎችም ለበዓሉ መልካም ምኞታቸውን የገለጹ ኤምባሲዎች ናቸው።

በተያያዘም የተባበሩት መንግግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲል መልካም ምኞቱን ገልጿል።

1447ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በመላው ኢትዮጵያ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review