አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ

You are currently viewing አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ

AMN- መጋቢት 13/2018 ዓ.ም

በበኩረ ስዩማን ኢጃራ ግርማ የተጻፈዉ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ የተሰኘ ርዕስ የተሰጠዉ መጽሐፍ ተመርቋል፡፡ መጸሐፉ የአቡነ ጴጥሮስን ከልጅነት እስከ መስዋትነት የሚተርክ መሆኑን በኩረ ስዩማን ገልጸዋል።

መጽሐፉ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ነዉ የተጻፈዉ። በመርሐ ግብሩ ላይ የሃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል።

የመጽሐፉ ደራሲ በኩረ ስዩማን ኢጃራ ግርማ በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ የጦር መሳሪያ ሳይታጠቁ በሃይማኖትና በሀገር ፍቅር ጽናት ለጠላት አይበገሬ መሆን እንደሚቻል ማሳያ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ለሀገር መስዋዕት ሆነው ሀገርን አጽንተው ያቆዩትን የሀገር ባለውለታ የሚዘክረው ይኸው መጽሐፍ፣ የኢትዮጵያ የጥንካሬ ተምሳሌት ለትውልዱ የጀግንነት ታሪክ ስንቅ እንደሚሆንም ጸሐፊው ተናግረዋል።

በአልማዝ ሙሉጌታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review