AMN መጋቢት 13/2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የስራ ዕድልን የፈጠረ ነው ሲሉ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ በፍራፍሬ እና በደን ዛፎች የተከበበው የ ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ጉብኝትን አስመልክቶ ባሰፈሩት መልዕክት ሎጁ ለአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ያለው ቅርበት የጎብኝዎችን ምቾት ከመጨመሩም በላይ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የስራ ዕድልን የፈጠረ ነው ሲሉ ገልጸዋል።