ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚደረገው የመጀመሪያ ዙር የገንዘብ ድጋፍ ለፓርቲዎች ተከፋፈለ

You are currently viewing ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚደረገው የመጀመሪያ ዙር የገንዘብ ድጋፍ ለፓርቲዎች ተከፋፈለ

AMN- መጋቢት 14/2018 ዓ.ም

ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚደረገው የመጀመሪያ ዙር የገንዘብ ድጋፍ ለፓርቲዎች መከፋፈሉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩዎች በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚቀመጡበትን ተራ ቁጥር ለመወሰን የእጣ ማውጣት መርሐ ግብር እያከናወነ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በእጣ ማውጣት መርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት ቦርዱ የምርጫውን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከመንግስት የሚደረገው የመጀመሪያ ዙር 30 በመቶ የገንዘብ ድጋፍም ለሁሉም ፓርቲዎች እኩል መከፋፈሉን ሰብሳቢዋ ተናግረዋል።

የድምፅ መስጫ ወረቀቱ የፓርቲዎችን እና የግል እጩዎችን ስም፣ የምርጫ ምልክት እና ምስል በእጣ ተራ ቁጥራቸው መሠረት በቅደም ተከተል የሚይዝ ይሆናል።

በካሳሁን አንዱዓለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review