የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከኢራን ጋር ስምምነት ሊደረስ እንደሚችል ተናገሩ

You are currently viewing የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከኢራን ጋር ስምምነት ሊደረስ እንደሚችል ተናገሩ

AMN መጋቢት 14/2018 ዓ.ም

የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕ በአሜሪካና ኢራን መካከል ንግግር መደረጉንና ዋና የስምምነት ነጥቦች ዙሪያ ከመግባባት እንደሚደረስና ጦርነቱን የሚያስቆም ስምምነት ሊፈፀም እንደሚችል ተናገሩ።

የመካከለኛው ምስራቅ መልዕክተኛ ስቴቭ ዊትኮፍ እና የቅርብ ደጋፊያቸው ጄርድ ኩሽነር ከኢራናውያን ጋር መወያየታቸውንና ውይይቱ ዛሬም እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ፕሬዛደንት ዶናልድ “ ጠንካራ ንግግር አድርገናል ፥ ወዴት እንደሚመሩን እናያለን ፥ ያስቀመጥናቸው የስምምነት ነጥቦች አሉን በሁሉም ላይ ጠንካራ ንግግር አድርገናል ” ማለታቸውን ሮይተርስ በዘገባው ጠቅሷል። እውነተኛ ስምምነት ለመፈፀም እንዲቻል ከፍተኛ ጥረት ላይ ነን ሲሉ ለሪፖርተሮች መናገራቸውን ነው ዘገባው የጠቀሰው።

ፕሬዘዳንቱ ከኢራን የትኛው ባለስልጣን ጋር ንግግር እያደረጉ እንደሆነ ከመግለጽ የተቆጠቡ ሲሆን ፥ በደፈናው በጣም የተከበረና መሪ ከሆነ ሰው ጋር ነው እየተነጋገርኩ ያለሁት ብለዋል።

የኢራኑ ፋርስ ዜና አገልግሎት ግን ከአሜሪካ ጋር ቀጥታም ሆነ ቀጥተኛ ያልሆነ ግንኙነት አለመደረጉን ምንጭ ጠቅሶ ዘግቧል።

በታደሰ ሽፈራዉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review