ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ባለፉት ሰባት ዓመታት የሰላማዊና በሀሳብ ላይ የተመሰረተ ትግል ቀንዲል ሆኖ ቆይቷል- ወ/ሮ ለይላ አሊ

You are currently viewing ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ባለፉት ሰባት ዓመታት የሰላማዊና በሀሳብ ላይ የተመሰረተ ትግል ቀንዲል ሆኖ ቆይቷል- ወ/ሮ ለይላ አሊ

AMN- መጋቢት 15/2018 ዓ.ም

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ባለፉት ሰባት ዓመታት የሰላማዊና በሀሳብ ላይ የተመሰረተ ትግል ቀንዲል ሆኖ ቆይቷል ሲሉ የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ለይላ አሊ ገለጹ፡፡

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ማኒፌስቶ ይፋ ማድረጊያ መርሐ ግብር እና የፓርቲውን 7ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በአድዋ ድል መታሰቢያ አካሂዷል።

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን እያከናወኑ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሆነው ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ የተመሰረተበትን 7ኛ ዓመት በዓል እያከበረ ይገኛል።

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ፤ ያዘጋጀውን የምርጫ ማኒፌስቶ በዚሁ መድረክ ላይ ይፋ አድርጓል። ማኒፌስቶው አምስት ክፍሎችን ስለመያዙ በመድረኩ ላይ ተብራርቷል።

የኢኮኖሚ ጉዳዮች፣ ማኅበራዊ ጉዳዮች፣ ፖለቲካዊ ጉዳዮች፣ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ እና የማኒፌስቶ ትግበራ የሚሉት የፓርቲው የምርጫ ማኒፌስቶ የያዛቸው ክፍሎች እንደሆኑም ተመላክቷል።

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በርከት ያሉ እጩዎችን ካስመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንደኛው እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በበላይሁን ፍስሃ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review