በተለያዩ ክልሎች የየአካባቢውን ባህልና ቁሳቁስ ያገናዘቡ የሞዴል ቤቶች ግንባታ እየተካሄዱ ነዉ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing በተለያዩ ክልሎች የየአካባቢውን ባህልና ቁሳቁስ ያገናዘቡ የሞዴል ቤቶች ግንባታ እየተካሄዱ ነዉ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN — መጋቢት 16/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቃና ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት ስላለው “የገጠር ኮሪደር ልማት” ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ይህ ፕሮጀክት በከተሞች እየተከናወነ ካለው የኮሪደር ልማት ጋር እጅግ የተቆራኘና የገጠሩን ማህበረሰብ የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ አሁን ያለው የገጠር አኗኗር ዘይቤ ለአርሶ አደሩ ምቹ አይደለም። በተለይም የሰውና የከብቶች በአንድ ቤት ውስጥ መኖር፣ የኃይል አቅርቦት እጥረት እና የማህበራዊ አገልግሎቶች ተደራሽ አለመሆን ታዳጊዎች ገጠሩን ጥለው ወደ ከተማ እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል።

ኑሮ እዛ እንዲመች ማድረግ ካልቻልን ሰው ባለበት እንዲቆይ ማድረግ አንችልም፤ ሰው ሸሸ ማለት ደግሞ ያልተዘጋጁ ከተሞች ላይ ጫና መፍጠርና የግብርናው ዘርፍ ወራሽ ማጣት ማለት ነው” ብለዋል።

የገጠር ኮሪደር ልማት ዋና ትኩረቶች የሰውና የከብቶች መኖሪያን የሚለዩ፣ በየአካባቢው በሚገኙ ግብዓቶች የሚገነቡ ሞዴልናዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች መገንባት ፣ በሶላር ኢነርጂ እና በባዮ ጋዝ አማካኝነት እናቶች ከጢስና ከእንጨት ለቀማ እንዲላቀቁ ማድረግየንጹህ ኢነርጂ አቅርቦት ማረጋገጥ ።

በጓሮ አትክልት፣ በወተትና በዶሮ እርባታ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እና ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ቴሌኮም እና የመብራት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል በማደራጀት አርሶ አደሩ የከተማን ምቾት ባለበት እንዲያገኝ በማድረግ የከተማ አገልግሎቶችን ወደ ገጠር ማምጣት ነው ።

የገጠር ኮሪደር ከክትመት ጋር እንደማይቃረን ይልቁንም ከተሞችን ከተጨማሪ ጫና እንደሚታደግ አስረድተዋል። ከተሞች ለታቀደላቸው የህዝብ ቁጥር ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ፣ የገጠሩ ማህበረሰብ ባለበት እንዲጸናና እንዲበለጽግ ማድረግ የግድ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ክልሎች የየአካባቢውን ባህልና ቁሳቁስ ያገናዘቡ የሞዴል ቤቶች ግንባታ መጀመሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ስራው በህዝቡ ዘንድ ትልቅ ደስታን መፍጠሩን ጠቁመዋል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review