AMN መጋቢት 16/2018 ዓ.ም
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ማሪያ ትሪፖዲ ጋር በመሆን ከእንጦጦ እስከ አራዳ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን በጎብኘታቸዉን ገለጹ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ከሚገኘው የመጀመሪያው የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን ፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ መልሶ ማልማት ፎረም ጎን ለጎን፣ ከጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ማሪያ ትሪፖዲ ጋር በመሆን ከእንጦጦ እስከ አራዳ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ጎብኝተናል ብለዋል፡፡
ከማሪያ ትሪፖዲ ጋር ለነበረን ፍሬያማ ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
