የጋራ ምክር ቤቱ የምርጫ ስነ ምግባር ላይ ለአባላቱ ስልጠና ሰጠ

You are currently viewing የጋራ ምክር ቤቱ የምርጫ ስነ ምግባር ላይ ለአባላቱ ስልጠና ሰጠ

AMN — መጋቢት 17/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 7ኛው አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነጻና ዲሞክራያዊ ሆኖ አንዲጠናቀቅ የሚያግዝ የምርጫ ስነ ምግባር ስልጠና ለአባለቱ ሰጠ።

ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመተባባር የተዘጋጀው ይህ ስልጠና የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ሂደት ወቅት ሊከተሏቸው በሚገቡ ህጎች ፣መመሪያዎች እና የስነ ምግባር ደንቦች ላይ ሰፊ ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡

ስልጠናው የሚታዩ የህግ ክፍተቶችን በመሙላት ፓርቲዎች መብትና ግደታቸውን ለይተው እንዲያወቁ ማስቻሉም ተገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ ምርጫው ፍትሃዊ እንዲሆን በትኩረት እንደሚሰራ የገለፀ ሲሆን ፣ በፓርቲዎች መካካል ጤናማ የሆነ ፉክክር እና ትብብር እንዲኖር ጥሪ ቀርቧል።

የጋራ ምክር ቤቱ ምርጫውን ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ መሆኑንም ገልጿል፡፡

ቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review