ትምህርት እና ጤና – የአራተኛዉ ዙር የAMN የምርጫ ክርክር መድረክ ልዩ ትኩረት

You are currently viewing ትምህርት እና ጤና – የአራተኛዉ ዙር የAMN የምርጫ ክርክር መድረክ ልዩ ትኩረት

AMN – መጋቢት 17/2018

በ7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ላይ የሚሳተፉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ላይ ቀርበዉ በማህበራዊ ጉዳይ በተለይም በትምህርት እና ጤና ፖሊሲ ላይ የሀሳብ ሙግት አድርገዋል፡፡

በክርክር መድረኩ ላይ 4 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች

1. ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት

2. ህዳሴ ፓርቲ

3. ብልፅግና ፓርቲ

4. ኢዜማ ፓርቲ ተሳትፈዋል፡፡

በክርክር መድረኩ ላይ ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት መሰረት የሆነውን የትምህርት ዘርፍ በቀጣዮቹ 5 ዓመታት የሚመሩበትን ፖሊሲ እና ማኒፌስቶዎቻቸውን አቅርበዋል።

የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት፣ የማለፍ ምጣኔ፣ የትምህርት ቋንቋ እና የተማረ የሰው ኃይል ጥራት እና ተወዳዳሪነት ላይ ብርቱ ሙግት ተካሄዷል።

ጤናማ ዜጋን በማፍራት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ወረርሽኝ እና ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ከመከላከልና ከማከም ጋር ተያይዞ የሚከተሉትን ፖሊሲ ለመራጩ ህዝብ አቅርበዋል።

የእናቶች እና ህፃናት ሞት ቅነሳ፣ መድሃኒት አቅርቦት፣ የጤና ተቋማት ተደራሽነት በተመለከተ ፓርቲዎቹ የሚከተሉትን የፖሊሲ አቅጣጫ ላይ በሃሳብ ተከራክረዋል።

ኤኤምኤን ይህንን የምርጫ ክርክር በቅርብ ቀን በአዲስ ሚዲያ ኔታዎርክ የሚዲያ አማራጮች ለአድማጭ ተመልካቾቹ ያቀርባል፡፡

በተገኝ በፍቃዱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review