በነዳጅ ምርቶች ግብይት ላይ ስለሚፈጸሙ ህገ-ወጥ ድርጊቶችና የሚያስከትሏቸው ጠንካራ የወንጀል ቅጣቶችን ምን ያህል ያውቃሉ?

You are currently viewing በነዳጅ ምርቶች ግብይት ላይ ስለሚፈጸሙ ህገ-ወጥ ድርጊቶችና የሚያስከትሏቸው ጠንካራ የወንጀል ቅጣቶችን ምን ያህል ያውቃሉ?

AMN- መጋቢት 18/2018 ዓ.ም

የነዳጅ ምርቶች የግብይት ስርዓትን ለመደንገግ በወጣው አዲስ አዋጅ ቁጥር 1363/2017 መሰረት፣ በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመግታት የሚያስችሉ ጠንካራ የቅጣት እርምጃዎች መዘርጋታቸው ይታወቃል።

በአዋጁ መሰረት በዋናነት የተለዩት ወንጀሎችና ቅጣቶች የሚከተሉት ናቸው፦

1. ህገ-ወጥ ክምችትና የግብይት ስርዓትን መጣስ

የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ያከማቸ ወይም ከግብይት ስርዓቱ ውጭ ሲሸጥ የተገኘ ማንኛውም ሰው፦

👉 የተያዘው ነዳጅ እንዲወረስ ይደረጋል፤

👉ከ3 እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና፤

👉ከ350 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል።

2. ነዳጅን ከባዕድ ነገር ጋር መቀላቀል

የነዳጅ ውጤቶችን ሆን ብሎ ከባዕድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል ለግብይት የሚያቀርቡ ግለሰቦች፦

👉 ነዳጁ እንዲወገድ ተደርጎ ከ 5 እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት፤

👉ከ 350 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይጠብቃቸዋል።

3. ከመደበኛው የዋጋ ተመን በላይ መሸጥ

መንግስት ከተመነው የመሸጫ ዋጋ በላይ የሚሸጡ የግብይት ተዋናዮች፦

👉 ለመጀመሪያ ጊዜ ጥፋት፦ ከ300 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር መቀጮ፤

👉ለተደጋጋሚ ጥፋት፦ ከ3 እስከ 5 ዓመት ጽኑ እስራት እና ከ300 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር መቀጮ።

4. የኮንትሮባንድና የማጓጓዣ መስመር ጥሰት

ነዳጅን ከተፈቀደው መስመር ውጭ ማጓጓዝ፣ ካልተፈቀደ ቦታ ማራገፍ ወይም ወደ ጎረቤት ሀገር በኮንትሮባንድ ማሸጋገር፦

👉ነዳጁ ተወርሶ ከ 5 እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት፤

👍 ከ400 ሺህ እስከ 700 ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ያስቀጣል።

5. የቴክኒክና የዲጂታል አሰራር ማጭበርበር

👉የልኬት መሣሪያዎች (ሜትር) ማጭበርበር፦ ፕሎምፕ የቆረጠ ወይም ልኬት ያዛባ ከ 3 እስከ 7 ዓመት ጽኑ እስራትና እስከ 500 ሺህ ብር መቀጮ።

👉 የዲጂታል ስርዓት መጣስ፦ እስከ 2 ዓመት እስራትና እስከ 300 ሺህ ብር መቀጮ።

ህጉ በዋናነት የታለመው በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ያለውን ህገ-ወጥ የነዳጅ ዝውውር ለመግታትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሲሆን፤ በተለይም የዲጂታል ግብይት ግዴታ መደረጉ ለቁጥጥሩ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

በዘርፉ ላይ የተሰማሩ የንግዱ ማህበረሰብ አባላትም ሆኑ ግለሰቦች፣ አዋጁን አክብረው በመስራት ራሳቸውን ከእስራትና ከከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ መጠበቅ ይገባል።

የህግ የበላይነትን ማክበር የሁሉም ግዴታ ነው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review