ከኢራን ጋር የሚደረገው ንግግር በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው- ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

You are currently viewing ከኢራን ጋር የሚደረገው ንግግር በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው- ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

AMN- መጋቢት 18 /2018ዓ.ም

አሜሪካ፣ ከኢራን ጋር እየተደረገ ያለው ንግግር እንደቀጠለ በመሆኑ፣ ለቀጣይ 10 ቀናት የኃይል ተቋማቷን ከመደብደብ እንደምትቆጠብ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ተናገሩ።

ከኢራን ጦርነት በኋላ ትናንት የመጀመሪያ የካቢኔ ስብሰባቸውን ያደረጉት ፕሬዚዳንቱ፣ የኢራን አየር ኃይልና ባሕር ኃይል “ሙሉ ለሙሉ” ማንኮታኮታቸውንና 90 በመቶ ሚሳኤሎቿ ማለቃቸውን ገልፀዋል።

ኢራን ስምምነት እንዲደረስ እየለመነች ነው ያሉት ዶናልድ ትረምፕ፣ ድርድሩን ካላደረገች አሜሪካ ማጥቃቷን ትቀጥላለች ማልታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የካቢኔ ስብሰባውን የተሳተፉት የአሜሪካ መካከለኛው ምሥራቅ ልዩ መልዕክተኛ ስቴቭ ዊትኮፍ፣ የአሜሪካ ባለ 15 ነጥቦች መደራደሪያ በፓኪስታን በኩል ለኢራን መላኩን ገልፀዋል።

የኢራኑ መህር ኒውስ እንደዘገበው ኢራን የአሜሪካን መደራደሪያ ውድቅ አድርጋለች።

ጦርነቱ የሚያልቅበትን ሁኔታና ጊዜን አሜሪካ መወሰን አትችልም ያለው ዘገባው፣ ኢራን የራሷን 5 ቅድመ ሁኔታዎች ማስቀመጧን ጠቅሷል።

በታደሰ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review