“የዝሆኖች ትግል ለሣሮች ጠንቅ” እንደሆነዉ ሁሉ፤ አንድ ብቸኛ ኃይል ለመፍጠር የሚደረገዉ የኃያላን ፍልሚያና ትግል፤ የአዳጊ ሃገራትን የመልማት መሻት አቀበት አድርጎታል፡፡
ለአንዱ ኃይል ደጋፊ መሆን እንጂ ለራስ ኃይል መሆንን የማይፈቅድ ሆኗል፡፡ በአንድ አስተሳሰብ መጠቅለልና ማደር ብቸኛ አማራጭ እየሆነ ነዉ፡፡
”በእኔ በኩል ያልተሰለፈ፤በሌላ በኩል እንደተሰለፈ ይቆጠራል” በሚል አንድምታ የሚመራዉ ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት፤ ድኾችን የበለጠ ያደኽያል፡፡ ባለጠጎችን ደግሞ ከልክ በላይ ያበለጽጋል፡፡ በዚህ ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ መድረክ የተያዘዉ የአዳጊ ሀገሮች ህልዉና አደጋ ዉስጥ ገብቷል፡፡
ከድህነት ለመላቀቅ የሚያደርጉት ጥረት በፖለቲካዊ ስልቶች በየጊዜዉ ይናጋባቸዋል፡፡ ዕድገታቸዉን ወደ ተስፋ አስቆራጭ አዙሪት ይቀይርባቸዋል፡፡ – የመደመር መንግሥት – ገጽ 341የዓለማችን የኃያልነት ሩጫ ” ትንሹ ዓሣ ትልቁ ዓሣ የሚሰለቅጥበት“ አካሄድ ነዉ፡፡
“የዝሆኖች ትግል ለሣሮች ጠንቅ” እንደሆነዉ ሁሉ፤ አንድ ብቸኛ ኃይል ለመፍጠር የሚደረገዉ የኃያላን ፍልሚያና ትግል፤ የአዳጊ ሃገራትን የመልማት መሻት አቀበት አድርጎታል፡፡ ለአንዱ ኃይል ደጋፊ መሆን እንጂ ለራስ ኃይል መሆንን የማይፈቅድ ሆኗል፡፡ በአንድ አስተሳሰብ መጠቅለልና ማደር ብቸኛ አማራጭ እየሆነ ነዉ፡፡
”በእኔ በኩል ያልተሰለፈ፤በሌላ በኩል እንደተሰለፈ ይቆጠራል” በሚል አንድምታ የሚመራዉ ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት፤ ድኾችን የበለጠ ያደኽያል፡፡ ባለጠጎችን ደግሞ ከልክ በላይ ያበለጽጋል፡፡ በዚህ ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ መድረክ የተያዘዉ የአዳጊ ሀገሮች ህልዉና አደጋ ዉስጥ ገብቷል፡፡ ከድህነት ለመላቀቅ የሚያደርጉት ጥረት በፖለቲካዊ ስልቶች በየጊዜዉ ይናጋባቸዋል፡፡ ዕድገታቸዉን ወደ ተስፋ አስቆራጭ አዙሪት ይቀይርባቸዋል፡፡ – የመደመር መንግሥት – ገጽ 341