ታሪክ አሻጋሪው ስምምነት

You are currently viewing ታሪክ አሻጋሪው ስምምነት
  • አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የዓድዋን ድል ታላላቅ ታሪኮች ለዓለም በማስተዋወቅ እና ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና እያበረከተ እንደሚገኝ ተመላክቷል

ከተሞች የሕዝብ መኖሪያ ብቻ አይደሉም፤ የሀገርን የሥልጣኔ ደረጃ የሚለኩ፣ የኢኮኖሚውን የልብ ትርታ የሚያሳዩና የዜጎችን የነገ ተስፋ የሚሰንቁ ሕያው ምስሎች እንጂ። አንድን ሀገር እንደ ሰው ብንመስለው፣ ከተሞች የዚያ አካል ‘እጅና አእምሮ’ ናቸው። በዕቅድና በጥበብ የሚመሩበት አዕምሮ፣ የልማትና የሥራ ዕድል የሚፈጠርባቸው ጠንካራ እጆችም ጭምር ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እንደሚገልጹት፣ ከተሞች የሀገር እጅና አዕምሮ እንዲሁም የሀገር መኳያ ናቸው።

ዛሬ ላይ በከተሞች የሚገነቡ ታላላቅ ሜጋ ፕሮጀክቶችና የውበት መገለጫዎች ደግሞ ተራ የግንባታ ውጤቶች ብቻ አይደሉም። እነዚህ ፕሮጀክቶች የከተማን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ የነዋሪዎችን ማኅበራዊ ትስስር የሚያጠናክሩ፣ ለቱሪዝም መስህብነት የሚመቹና ከተሞች ‘የሀገር መኳያ’ ሆነው እንዲወጡ የሚያስችሉ የለውጥ ሞተሮች ናቸው። ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ደግሞ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ቀዳሚው ነው።

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ከተሞች ‘የልማት እጅ’ መሆናቸውን በተግባር ያሳየ ደማቅ አሻራ ስለመሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ የከተማዋን ውበትና ግርማ ሞገስ ከመጨመር ባለፈ፣ ለቱሪዝም፣ ለጥናትና ምርምር እንዲሁም ለተለያዩ ማኅበራዊ መስተጋብሮች ሰፊ በር በመክፈት የከተማዋን ሁለንተናዊ ፋይዳ ከፍ አድርጎታል። እንደነዚህ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በከተማ ውስጥ መገንባታቸው፣ ከተሞች የሀገር መለያና የሥልጣኔ መድረክ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሲሆን፤ ነዋሪዎችም በከተማቸው ታሪክና ዕድገት እንዲኮሩ፣ የነገዋን ዘመናዊት ኢትዮጵያን በልበ-ሙሉነት እንዲያልሙ ትልቅ ሥነ-ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ስንቅ ይሆንላቸዋል ማለት ይቻላል።

መገናኛ ብዙኃን ደግሞ የከተማ ፕሮጀክቶችን ታሪክና ፋይዳ ለሕዝብ ተደራሽ በማድረግ ረገድ እንደ መስታወት ሆነው ያገለግላሉ። እንደ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ያሉ ፕሮጀክቶችም ካላቸው ግዝፈት አንጻር፣ ሚዲያው የህንፃዎቹን ውበት ብቻ ሳይሆን በስተጀርባ ያሉትን ኢኮኖሚያዊ፣ ታሪካዊና ማኅበራዊ ጠቀሜታዎች በዝርዝር በመተንተን ዜጎች በልማቱ ላይ ባለቤትነት እንዲሰማቸው ያደርጋል። ይህም በሕዝብና በመንግሥት መካከል ጠንካራ የመረጃ ድልድይ በመገንባት፣ ፕሮጀክቶቹ የሀገር ኩራትና የሥልጣኔ መገለጫ መሆናቸውን በሰፊው በማስተዋወቅ ረገድ የማይተካ ሚና ይጫወታሉ።

የዓድዋ ድል ለጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ፋና፣ ለኢትዮጵያውያን ደግሞ የጽናት ማኅተም ነው። ሆኖም ይህ ግዙፍ ታሪክ ትርጉሙ ጎልቶ የሚወጣውና ለትውልድ የሚሻገረው በዘመኑ ቋንቋ ተቀርጾና ተሰንዶ ሲቀርብ ጭምር ነው። አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ይህንን ታሪካዊ ኃላፊነት ተረክቦ የጥቁር ሕዝቦች ድል የሆነውን የዓድዋን ገድል በተንቀሳቃሽ ምስልና በፊልም ለማሰናዳት ከሰሞኑ ስምምነት ተፈራርሟል።

ይህ ስምምነት የከተማዋን ታሪክ መዘክር ብቻ ሳይሆን፣ በየዕለቱ የሚታይና የሚሰማ የሥልጣኔ ትርክት ማዕከል ያደርጋታል። ሚዲያውና ሙዚየሙ የተፈራረሙት ይህ ውል፣ ሙዚየሙን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታይ የኪነ-ጥበብ ፈርጥ የማድረግ ታላቅ የከተማ ግንባታ ሥራ አካል ነው።

የጥቁር ሕዝቦች ድል የሆነው የዓድዋ ድል ታሪክ በተንቀሳቃሽ ምስል ወይም በፊልም ተሰንዶ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከባለድርሻ አካላት ጋር ትብብር እንደሚሰራም የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገልጸዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ፣ ኤ ኤም ኤን የዓድዋን ድል ታላላቅ ታሪኮች አጉልቶ ከማውጣት፣ ለተቀረው ዓለም ከማስተዋወቅ እና ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ ከማድረግ ረገድ በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የመዲናዋ ፈርጥና የቱሪዝም መስህብ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ግንባታ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ እና ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ በኋላም የዓድዋን ታሪኮች በተለያዩ ቋንቋዎች ለሕዝቡ ተደራሽ በማድረግ እና የጋራ ታሪክን በማጽናት ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ መሆኑን ገልጸዋል የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን። አክለውም፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ የዓድዋ ድል ታሪክ በአግባቡ ተሰንዶ ለቀጣይ ትውልድ የሚተላለፍበት ስፍራ መሆኑንም አስረድተዋል።

የዓድዋ ድል ታሪክ በተንቀሳቃሽ ምስል ወይም በፊልም ተሰንዶ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ ከማድረግ አንጻር የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ፣ ምሁራን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ሊሠሩ ይገባል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ኤ ኤም ኤንም ኃላፊነቱን እንደሚወጣ ገልጸዋል።

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ቤኮ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ አባቶቻችን ትልቅ ዋጋ ከፍለው የተከበረች ሀገር አውርሰውናል፤ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክም ይህንን ታሪክ አጉልቶ ከማውጣት፣ ለተቀረው ዓለም ከማስተዋወቅና ለትውልድ እንዲተላለፍ ከማድረግ ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ፓን አፍሪካኒዝም፣ ዓድዋና ሕዳሴ የማይለያዩ ጉዳዮች ናቸው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እነዚህን የወል ታሪኮች በማስተዋወቅ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ሲሉ ይገልጻሉ። ሁለቱ ተቋማት የበለጠ ተቀራርበው ለመሥራት የሚያስችላቸውን ፊርማ ማኖራቸውም ለከተማዋ ብሎም እንደ ሀገር ለተያዙ ትልሞች የሚጫወተው ሚና የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየሙ ጥምረት ከተሞች ‘የሀገር እጅና አዕምሮ’ ናቸው ለሚለው እሳቤ ተግባራዊ ማሳያ ነው። የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየሙ እንደ ‘እጅ’ የታሪኩን አሻራ ጨብጦ ሲይዝ፣ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ደግሞ እንደ ‘አዕምሮ’ ታሪኩን ተንትኖና አቀናጅቶ ለዓለም ያሰራጫል።

በፊልም የታገዘ ሰነድ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፍ የማይደበዝዝ የታሪክ ቅርስ ከመሆኑም ባለፈ፣ አዲስ አበባን በዓለም አቀፍ የቱሪዝም ካርታ ላይ የጥቁር ሕዝቦች የክብር መዳረሻ አድርጎ ይስላታል። የከተማ ፕሮጀክቶች ፋይዳቸው የሚጎላው እንዲህ ካሉ የሚዲያ ሥራዎች ጋር ሲጋቡ መሆኑን ስንመለከት፣ ይህ ስምምነት ከተማዋን ‘ለመኳል’ የተጀመረው ጉዞ አንድ እርምጃ ወደፊት መራመዱንና የታሪካችን ድምፅ በምስል ታጅቦ ዓለምን እንዲያነጋግር በር መክፈቱን ያረጋግጣል።

በእርግጥ ይህ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ እና በዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም መካከል የተደረገው ስምምነት አዲስ ክስተት ሳይሆን፣ ተቋሙ ላለፉት ዓመታት ከተለያዩ ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር ሲያከናውናቸው የቆያቸው ስኬታማ ትብብሮች ቀጣይ አካል ነው። አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከዚህ ቀደም ከከተማዋ ታላላቅ የልማት ተቋማት ጋር በመቀናጀት፣ የከተማዋን ሜጋ ፕሮጀክቶች ገጽታ ለነዋሪውና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በማስተዋወቅ ረገድ ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል።

ለአብነት ያህል፣ ተቋሙ ከአዲስ አበባ ሜጋ ፕሮጀክቶች ቢሮ ጋር በመሆን እንደ መስቀል አደባባይ ያሉ ግዙፍ ግንባታዎችን ሂደት ከመጀመሪያው እስከ ፍጻሜው በመዘገብ፣ የፕሮጀክቶቹን ምህንድስናና ማኅበራዊ ፋይዳ ለሕዝብ ግልጽ አድርጓል። በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመቀናጀት ‘እንኳን ደህና መጡ’ በሚሉና መሰል የቱሪስት መዳረሻዎችን በሚያስተዋውቁ ፕሮጀክቶች ላይ በጋራ በመሥራት፣ የከተማዋን የቱሪዝም ፍሰት ለማሳደግ ጉልህ ሚና ተጫውቷል።

እንደዚሁም ከጤና እና ከትምህርት ቢሮዎች ጋር የሚደረጉት ዘላቂ የሚዲያ ስምምነቶችም ተቋሙ የልማት አጋርነቱን በተግባር ያረጋገጠባቸው ማሳያዎች ናቸው። እነዚህ የተከማቹ ልምዶች አሁን ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ጋር ለተጀመረው የታሪክ ሰነድ ዝግጅት እንደ ትልቅ ግብዓት የሚያገለግሉ ሲሆን፣ የሚዲያ ተቋሙ ካለው ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አቅም ጋር ተዳምሮ የዓድዋን ታሪክ በላቀ ጥራትና ጥልቀት ለማቅረብ ዋስትና ይሆናሉ።በሳህሉ ብርሃኑ

እንደዚሁም ከጤና እና ከትምህርት ቢሮዎች ጋር የሚደረጉት ዘላቂ የሚዲያ ስምምነቶችም ተቋሙ የልማት አጋርነቱን በተግባር ያረጋገጠባቸው ማሳያዎች ናቸው። እነዚህ የተከማቹ ልምዶች አሁን ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ጋር ለተጀመረው የታሪክ ሰነድ ዝግጅት እንደ ትልቅ ግብዓት የሚያገለግሉ ሲሆን፣ የሚዲያ ተቋሙ ካለው ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አቅም ጋር ተዳምሮ የዓድዋን ታሪክ በላቀ ጥራትና ጥልቀት ለማቅረብ ዋስትና ይሆናሉ።

በሳህሉ ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review