AMN — መጋቢት 20/2018 ዓ.ም
የቀጨኔና አካባቢው ገፅታ ዛሬ ሙሉ ለሙሉ ተቀይሯል። ቀደም ሲል የቆሸሸና ለምንም አገልግሎት የማይውል የነበረው የወንዝ ዳርቻ፣ ዛሬ ለነዋሪዎችና ለጎብኝዎች የመዝናኛ ስፍራ ለመዲናዋም ሌላ ድምቀት ሆኗል።
በአዲሱ የቀጨኔ ኮሪደር ልማት ምን ተለወጠ?
ከ20 ዓመት በላይ በነዋሪነት እና በስራ አካባቢውን የሚያውቁት ነዋሪዎች አሁን ላይ የገፅታ ለውጥ።
አካባቢው አረንጓዴ በመልበሱና በወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች በመታገዙ እንደ “አንድነት ፓርክ” ውብና ማራኪ ሆኗል ሲሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በተለያየ የማህበረሰብ ልማት ስራ አካባቢውን በቀድሞ ገፅታ የምታውቀው ሐዊ በዳሳ አሁን ላይ በዚህ መልኩ አምሮ : ተውቦ እና ተቀይሮ በማየቷ መደሰቷን ደስተኛ መሆኗን ትገልጻለች።
የውጭ ሃገር ዜጎች ጭምር የአካባቢውን ገፅታ ሲያዩ ለማመን እንደሚከብዳቸውና በለውጡ እጅግ መገረማቸውን ተናግራለች።
የባህል መገለጫ፡ የቀጨኔ ታዋቂ የሸማ ስራና የጥበብ ሙያ በልማቱ ውስጥ በልዩ የሞዛይክ ስራዎችና ቅርፃ ቅርጾች ተካቶ የባህል ማስታወሻነቱ እንዲጠበቅ ተደርጓል ።
አሁን ላይ አካባቢው ህፃናት በደስታ የሚቦርቁበትና የሚጫወቱበት፣ አዋቂዎች አእምሮአቸውን የሚያድሱበትና ነፋሻማ አየር የሚቀበሉበት ስፍራ ሆኗል የሚሉት ደግሞ ሌላኛው የአካባቢው ነዋሪ በርሌ ጋሻው ናቸዉ።
ለዓመታት የተከማቸን የቤት ሰራ በአንድ ዓመት እንዲህ ውብ አድርጎ መስራት የሚደነቅ ነው።

በአካባቢው የተሰራው የወንዝ ዳርቻ ልማት ውብ ገፅታ ከማላበሱ ባለፈ ለአካባቢው ነዋሪዎች ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር የኑሮ ጫናቸው እንዲቀንስና የተረጋጋ ህይወት እንዲመሩ ብሎም የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ እነዳስቻላቸው ተናግረዋል።
የአካባቢው ለውጥ የአዲስ አበባን መልካም ገፅታ ለውጭ ሀገር ዜጎች ጭምር በአዲስ መልክ እያስተዋወቀ ይገኛል።
ከፍታ ቦታ ላይ የምትገኘው ቀጨኔ፣ ከቀን ውበት ባለፈ የምሽት ገፅታዋ ይበልጥ ደምቋ።
በአካባቢው የሚገኙ ወንዞች ከዚህ ቀደም ለነዋሪዎች የጎርፍ አደጋ እና የጤና ስጋት የነበረው ታሪካቸው ተቀይሮ የበርካቶች ውብ ዓይን ማረፊ እንዲሆን ተሰርቶ ለውጤት በቅቷል።
ከዚህም ባሻገር የሀገርን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አደባባይ ከፍ አድርገው ያውለበለቡ ጀግኖች አትሌቶች በዚህ ሥፍራ ይዘከራሉ።
በያለው ጌታነህ