ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ማዕከል የሆነችውን ካርግ ደሴትን ለመያዝ እያሰቡ መሆኑ ተነገረ

You are currently viewing ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ማዕከል የሆነችውን ካርግ ደሴትን ለመያዝ እያሰቡ መሆኑ ተነገረ

AMN- መጋቢት 21 /2018 ዓ.ም

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ማዕከል የሆነችውን ካርግ ደሴትን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚቻል ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ከፋይናንሻል ታይምስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ አሜሪካ ደሴቷን በቀላሉ ልትይዛት እንደምትችል ገልጸዋል፡፡ ሆኖ ግን የሰላም ስምምነቱ ቀድሞ ሊደረስ እንደሚችልም አክለዋል።

በእስያ ገበያዎች የነዳጅ ዋጋ በአንድ በርሜል ከ 115 ዶላር በላይ ከፍ ባለበት በአሁኑ ወቅት ኢራን የአጸፋ ጥቃት እርምጃዋን በማስፋት የአሜሪካ እና የእስራኤል ባለስልጣናት መኖሪያ ቤቶችን እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎችን ኢላማ እንደምታደርግ አስፈራርታለች።

ኢራን የኢነርጂ መሰረተ ልማቶቿ በጥቃት መጎዳታቸውን ገልጻ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ በአብዛኛው የቴህራን ክፍሎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተመልሷል።

በሌላ በኩል እስራኤል በኢራን ጥቃት ምክንያት በአንድ የኢንዱስትሪ ማዕከል ላይ ተከስቶ የነበረው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቃለች።

የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀገራቸው በሚቀጥሉት ቀናት የሰላም ንግግር ለማስተናገድ እየተዘጋጀች መሆንዋን የተናገረች ቢሆንም ኢራን ወይም አሜሪካ በንግግሩ ላይ ስለመካፈላቸው ግን የታወቀ ነገር የለም።

አሜሪካ 3 ሺህ 500 ወታደሮችን እና የጦር መርከብ ወደ ቀጠናው መላኳን ተከትሎ፣ የኢራን ፓርላማ አፈ-ጉባኤ የአጸፋ እርምጃ ለመዉሰድ የአሜሪካንን የምድር ጦር እየጠበቅን ነው ማለታቸዉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review