ሐገራዊ የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል በሀረር ከተማ ተጀመረ

You are currently viewing ሐገራዊ የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል በሀረር ከተማ ተጀመረ

AMN – መጋቢት 20/2018 ዓ.ም

23ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድርና 19ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል በሀረር ከተማ በድምቀት ተጀመረ።

የባህል ስፖርቶች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ውድድሩና ፌስቲቫሉ ከመላው የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ 1500 ተሳታፊዎች በ11 የባህል ስፖርት አይነቶች ይሳተፋሉ።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መክዩ መሃመድ ፣ ባህላዊ ስፖርቶችን በአፍሪካ ብሎም በአለም አቀፍ መድረኮች ላይ ማስተዋወቅ ይገባል ብለዋል።

ለውድድሩና ፌስቲቫሉ ታዳሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የሐረሪ ክልል ፕሬዚደንት የሆኑት አቶ ኦርዲን በድሪ መድረኩ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ የባህል ስፖርት ተወዳዳሪዎች አንድነት የሚያንጸባርቁበት እና ኢትዮጵያነታቸውን የሚያሳዩበት መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚደንትና የአፍሪካ የባህል ስፖርቶች ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ወ/ሮ ህይወት መሃመድ፣ ውድድሩና ፌስቲቫሉ የወንድማማችነት ስሜትን ማጎልበትና ባህላዊ ስፖርቶችን ለማህበረሰቡ በሚገባ ማስተዋወቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመርሃግብሩ ላይ የአፍሪካ ባህላዊ ስፖርቶች ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ካይ ካማቱዋ (ዶ/ር) እና የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፓይዳሞ (ዶ/ር) ተገኝተዋል።

በዘላለም አቢይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review