AMN – መጋቢት 21/2018 ዓ.ም
የ3ዲ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የዜጎችን የቤት ፍላጎት ለማጣጣም በትኩረት እየሰራ መሆኑን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አስታውቋል፡፡
50ኛ ዓመት ምስረታ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን “የትናንት ዛሬና የነገ ጉዞ ማሳያ እውነታዎች ” በሚል መሪ ሀሳብ ትኩረቱን ያደረገ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የፓናል ውይይት አካሂዷል።
ኮርፖሬሽኑ የነበሩበትን ፈተናዎች በሪፎርሞች አሸንፎ ወደ ተሻለ ለውጥ መሻገሩን ያነሱት የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ረሻድ ከማል(ዶ/ር) አሁን ላይ እንደ ሀገር ለታቀዱት ሰፋፊ ፖሮጀክቶች ተቋሙ በሙሉ ቁመና ላይ ሆኖ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።
ዲጂታል ስራን መሰረት በማድረግ ኮሪፖሬሽኑ ባለፍት ጥቄት አመታት በርካታ የአሰራር ስርአትን እንደዘረጋ ያነሱትረሻድ ከማል( ዶ/ር) ከወራት በኋላ የሚጀምረው የ3D የግንባታ ቴክኖሎጂ ለተቋሙ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር አንስተዋል።
ተቋሙ በቴክኖልጂ እራሱን ለማዘመን ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ የሰው ሀይል ግምባታ ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህም ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል ብለዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ የዜጎችን የቤት አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የተናገሩት የኢፌዴሪ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት በዚህም ሀገርን መገንባት የሚያስችል መሰረት እየዘረጋ መሆኑን ተናግረዋል።
በፓናል ውይይቱም የተለያዩ ጥናታዊ ፁሁፎች የቀረቡ ሲሆን በእነዚህም ላይ ውይይቶች ተካሂደዋል።
በራሄል አበበ