አዲስ አበባን እንደ ስሟ ያደመቀው የመጋቢት 24 የድል አሻራ

You are currently viewing አዲስ አበባን እንደ ስሟ ያደመቀው የመጋቢት 24 የድል አሻራ

AMN- መጋቢት 24/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባን ገጽታ በመቀየርና ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ በማድረግ ረገድ የመጋቢት 24 የለውጥ ድል ቁልፍ ሚና መጫወቱን በድጋፍ ሰልፍና የማስ ስፖርት መርሃ ግብር የተሳተፉ በአራዳ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎቸ ተናገሩ ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንድሙ ኡመር ባስተላለፉት መልዕክት፣ የመጋቢት 24 ዕለቱ ለትውልድ ታሪክ፣ ለሃገር ደግሞ አዲስ ተስፋን የወለደ የወጣቶች ትግል ፍሬ ያፈራበት መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ወንድሙ አክለውም፣ ይህ ድል፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አበባ ለማድረግ ያስቻለና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚመራው የመደመር መንግሥት ወደ ኃላፊነት እንዲመጣ መንገድ የከፈተ መሆኑን አስታውሰዋል።

የተገኘውን ድል ከማስጀመር ባለፈ ዘላቂነቱን ማረጋገጥ ቁልፍ ተግባር መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው አስገንዝበዋል። ወጣቶችም የዛሬ ውሳኔያቸው ለነገዋ ኢትዮጵያ መሠረት መሆኑን ተገንዝበው በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ በበኩላቸው፣ መጋቢት 24 ቀደም ሲል ታይተው የማይታወቁ ድሎችን ለማብሰር ያስቻለና “ሰባራውን የፖለቲካ ሥርዓት” ከመጠገን ባለፈ ተቋማዊ አቋም እንዲያዝ ያስቻለ ታሪክ የተሠራበት ነው ብለዋል።

በመጋቢት 24 የለውጥ ፍሬዎች የታላላቅ ኢኮኖሚያዊ ድሎች መመዝገብ፣ የማይደፈሩ የሚመስሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መጀመርና መጠናቀቅ እንዲሁም የዓድዋ መታሰቢያን የመሰሉ የታሪክ አሻራዎች እውን መሆን መቻላቸውን ኃላፊው ገልጸዋል። አዲስ አበባን በሚመጥናት ልክ ከፍ ለማድረግ የተሰሩ ሥራዎችም የለውጡ ትሩፋቶች መሆናቸውን አክለዋል።

በተጨማሪም “የውኃ እስረኞች አንሆንም” በሚል በመደመር መንግሥት የተጀመረውን ጥረት፣ በውይይትና በፍትሐዊነት የመጠቀም ጉዳይን በቅርብ ጊዜ ውስጥ እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አቶ አሰግደው አንስተዋል ።

በሰልፉ ላይ የታደሙ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ከለውጡ ወዲህ በሀገሪቱና በከተማዋ ላይ እየታዩ ላሉ ከፍተኛ የልማትና የለውጥ ሥራዎች ዕውቅና በመስጠት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።

በአብዱሰላም አንሳር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review