መጋቢት- የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች፣ ሃይማኖቶች እና ማንነቶች እኩልነትና ነጻነት የተገጋገጠበት ወር

You are currently viewing መጋቢት- የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች፣ ሃይማኖቶች እና ማንነቶች እኩልነትና ነጻነት የተገጋገጠበት ወር

AMN- መጋቢት 23/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ ሃይማኖቶች፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎች እና ማንነቶች መገኛ ሀገር ነች፡፡

የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ልዩነታቸዉን አክብረዉ በጋራ ሲቆሙ ያቀዱትን መፈጸም እንደሚችሉ ትላንት አድዋ ላይ የዉጭ ወራሪ ሃይሎችን ድል በማድረግ፤ ዛሬ ደግሞ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዳር በማድረስ እና በማስመረቅ አረጋግጠዋል፡፡ የባህር በር ጥያቄዉንም በጋራ ለመመለስ በመትጋት ላይ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ለረጅም ዘመናት የሃይማኖት፣ የብሄር፣ የቋንቋ፣ የባህልና የማንነት ልዩነታቸዉን አክብረዉና አንድነታቸዉን ጠብቀዉ፣ ተከባብረዉና ተቻችለዉ በአብሮነትና በጋራ መኖር የቻሉ ወንድማማች ህዝቦች ናቸዉ፡፡ ዛሬም ይህንኑ አብሮ የመኖር ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶቻቸዉን አክብረዉና ጠብቀዉ በጋራ በመኖር ላይ ይገኛሉ፡፡

ከብዝሃነትና ከህብረብሄራዊ አንድነት ጀርባ ያለዉ እዉነታ ይህ ቢሆንም ባለፉት ረጅም ዓመታት በወንድማማች ህዝቦች መካከል የተሰራጩት ሃሰተኛ እና ነጠላ ትርክቶች እንደ ሃገር ጥላቻን፣ ልዩነትን፣ ግጭትን እና ዉድመትን ከመፍጠራቸዉም በላይ ለሃገረ መንግስት ግንባታዉ ትልቅ ፈተና ሆነዉ ቆይተዋል፡፡

ከሁሉም በላይ ያለፉት ሥርዓቶች በወንድማማች ህዝቦች መካከል የፈጠሯቸዉ ሃሰተኛና ነጠላ ትርክቶች የኢትዮጵያን ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እዉቅና ያሳጡ ከመሆናቸዉ ባሻገር የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች እኩልነትና ነጻነት እንዳይከበር ትልቅ ተጽእኖ አድርገዋል፡፡

ይህንን የዘመናት ስብራት የተገነዘበዉ የለዉጡ መንግስት ከምንም በላይ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች፣ ሃይማኖቶች እና ማንነቶች እኩልነትና ነጻነት እንዲረጋገጥ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የሚገባቸዉን የፖለቲካ ዉክልና እንዲያገኙ፣ ማንነታቸዉ እንዲታወቅ እና እዉነተኛ ፊዴራላዊ ሥርዓት እንዲገነባም ትልቅ መሰረት ጥሏል፡፡

ብሄር ብሔረሰቦች በቋንቋቸዉ እንዲማሩ እና እንዲተዳደሩ፣ ባህላቸዉን እንዲያሳድጉ፣ ሃይማኖታቸዉን በነጻነት እንዲያራምዱ፣ በአካቢያቸዉም ሆነ በሃገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ የልማትና የሰላም ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አስችሏል፡፡

ከአሁን ቀድም የነበረዉ የጠቅላይነትና የጨፍላቂነት እሳቤ በአብሮነትና በወንድማማችነት የተተካ ሲሆን ህብረብሄራዊ አንድነትና ብዝሃነትም ትክክለኛዉ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ መዲና የሆነችዉ አዲስ አበባም የበርካታ ብሄሮች እና ብሄረሰቦች መኖሪያ እንደመሆኗ መጠን እንደ ኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ ልማቱ ሁሉ በወንድማማችነትና በአብሮ መኖር መንፈስ የብዝሃነትና የህብረብሔራዊ አንድነት መገለጫ ሆናለች፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review