መጋቢት 24 ፤ አዲስ አበባን የሰላም ተምሳሌት ያደረገው የለውጥ ጉዞ

You are currently viewing መጋቢት 24 ፤ አዲስ አበባን የሰላም ተምሳሌት ያደረገው የለውጥ ጉዞ

AMN – መጋቢት 24/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ባለፉት 8 ዓመታት ካከናወነቻቸው መጠነ ሰፊ ሀገራዊ ሪፎርሞች መካከል አዲስ አበባ ላይ የተሰራው የሰላምና ጸጥታ ግንባታ ሥራ አንዱና ዋነኛው የ”መጋቢት ፍሬ” ሆኖ ተመዝግቧል።

የለውጡ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣበት ከመጋቢት ወር 2010 ዓ.ም ወዲህ በመዲናዋ የተከናወኑ ተቋማዊ እና መዋቅራዊ ሪፎርሞች መካከል አንዱ፣ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ፤ ለአለም አቀፍ ዲፕሎማቶችና እንግዶች አስተማማኝ መኖሪያ እንድትሆን አድርገዋታል።

አዲስ አበባ አሁን ላይ በዘመናዊ የደህንነት ካሜራዎች (CCTV) እና በዲጂታል መረጃ መረብ ክትትል የሚደረግባት ከተማ ሆናለች። ይህ ቴክኖሎጂ ወንጀልን ቀድሞ በመከላከልና የተፈጸሙ ወንጀሎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር ለማዋል በሚደረገው ስራ ውስጥ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ በሰው ኃይል፣ በስልጠና እና በትጥቅ እንዲደራጅ ተደርጓል። ከፖለቲካ ወገንተኝነት የጸዳ፣ ለህግና ለዜጎች ደህንነት የቆመ የፖሊስ ኃይል መገንባት በመቻሉ በከተማዋን አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን አድርጓል።

ነዋሪው ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እንዲሰራ በተደረገው ጥረት እና ማህበረሰቡን በማሳተፍ በተሰራው ስራ ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርንና የከተማ ስርቆትን በከፍተኛ ደረጃ እንደቀንስ ተደርጓል፡፡

አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና፣ ሦስተኛዋ የአለማችን የዲፕሎማሲ ከተማ እና የዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ፣ በመዲናዋ የሚሰፍነው ሰላም ለሀገር ገጽታ ግንባታ እና ለኢንቨስትመንት ፍሰት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሆኗል።

መጋቢቱ 24 በተገኘዉ ድል ፣ ከተማዋ በሌሊትም ሆነ በቀን ያለምንም ስጋት ሰዎች የሚንቀሳቀሱባት ደማቅ መዲና እንድትሆን አድርጓታል።

ኢትዮጵያ የጀመረችው የብልጽግና ጉዞ መሰረቱ ሰላም ነው፤ አዲስ አበባ ደግሞ የዚህ ሰላም ቀዳሚ ምስክር ሆና ቀጥላለች።

የከተማዋን ፖሊስ ሰራዊት በሰው ኃይል፣ በስልጠና እና በትጥቅ በማደራጀት ከፖለቲካ ወገንተኝነት የጸዳ እና ለህግ የበላይነት የቆመ እንዲሆን ተደርጓል።

በዚህም አዲስ አበባ ለ24 ሰዓት እንቅስቃሴ አስተማማኝ ሰላም ያላት ከተማ እንድትሆን አድርጓታል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review