የዜጎችን የኑሮ ጫና ለማቅለል በሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን መክፈት ተችሏል- የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

You are currently viewing የዜጎችን የኑሮ ጫና ለማቅለል በሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን መክፈት ተችሏል- የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

AMN- መጋቢት 28/2018 ዓ.ም

የዜጎችን የኑሮ ጫና ለማቅለል በመላው ሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ከ2ሺ አንድ መቶ በላይ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን መክፈት ስለመቻሉ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

በበዓል ሰሞን የሚስተዋለውን ሰው ሰራሽ የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር አምራቹን ከሸማቹ የማገናኘት ስራ እንደሀገር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፣ በዚህም በመላ ሀገሪቱ ባሉ ዋና ዋና ከተሞች የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችና ባዛሮች ተከፍተዋል ብለዋል፡፡

በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ትላልቅ የገበያ ማእከላትን ከመገንባት ጀምሮ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ዜጎች በተመጣጣኝ ዋጋ ምርት የሚያገኙባቸው መሰረተ ልማቶች ተገንብተዋል ያሉት ሚንስትሩ፣ ይህም የከተማ አስተዳደሩን ቁርጠኝነት ከማሳየትም ባሻገር ገበያን በማረጋጋት ረገድ አይተኬ ሚና አለው ብለዋል ፡፡

በዛሬው ዕለትም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተከፈተው የትንሳኤ ባዛርም የዚሁ አንዱ አካል መሆኑን አስተው፣ ለበዓሉ ፍጆታ የሚውሉ የእንስሳት ተዋጽኦዎችን ጨምሮ በርካታ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በበቂ ሁኔታ ወደ ገበያ በማቅረብ ዜጎች በዓሉን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲያሳልፉ ያለመ ነው ብለዋል ፡፡

እንደሀገር አሁን ላይ የምርት አቅርቦት ችግር የለም ያሉት ሚኒስትሩ፣ የነዳጅ ዋጋ መጨመርን ምክንያት በማድረግ ህገ-ወጥ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ላይ ቁጥጥር ከማድረግም ባሻገር ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም አሳስበዋል ፡፡

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review