በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት የተገነቡ 14 የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካዎች በግብዓት ራሳቸውን በመቻል አገልግሎታቸውን እያጠናከሩ ነው

You are currently viewing በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት የተገነቡ 14 የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካዎች በግብዓት ራሳቸውን በመቻል አገልግሎታቸውን እያጠናከሩ ነው

AMN – መጋቢት 28/2018 ዓ.ም

የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የገነባቸው የዳቦና ዱቄት ፋብሪካዎች፣ ራሳቸውን በግብዓት በመቻል ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት ይበልጥ ዘላቂ እያደረጉ ይገኛሉ።

ጽሕፈት ቤቱ ዘላቂ ልማትን ለማምጣት ካቀዳቸው ግዙፍ ሥራዎች መካከል አንዱ የሆኑት እነዚህ ፋብሪካዎች፤ በቀን 300 ሺህ ዳቦ እና 420 ኩንታል ዱቄት የማምረት አቅም አላቸው።

በአሁኑ ወቅት በ14 የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተገንብተው በአነስተኛ ዋጋ ለህብረተሰቡ ምርት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

ፋብሪካዎቹ በሙሉ አቅማቸው እንዲሠሩና የዋጋ ንረትን እንዲቋቋሙ ለማድረግ፣ ጽሕፈት ቤቱ “በግብዓት ራስን የመቻል” ስልትን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ለዚህም በፋብሪካዎቹ ዙሪያ የሚገኙ የእርሻ መሬቶችን በመጠቀም የስንዴ ምርት በስፋት እየተመረተ ነው።

በአፋር ክልል የሚገኘው “የሰመራ ብርሃን ዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካ” የዚህ ስኬት ማሳያ ሆኗል፡፡

ለሰመራ ብርሀን ዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካ ከተዘጋጀው 500 ሄክታር መሬት ውስጥ፣ በመጀመሪያው ዙር 100 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ በመዝራት 2 ሺህ ኩንታል የስንዴ ምርት ለማምረት ተችሏል፡፡

ይህ ተሞክሮ ፋብሪካው በራሱ የስንዴ ምርት ጥራት ያለው ዳቦና ዱቄት በተመጣጣኝ ዋጋ ለክልሉ ነዋሪዎች እንዲያቀርብ ትልቅ አቅም እንደፈጠረለት የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት መረጃ ያሳል።

ይህ በሰመራ የታየው ውጤት፣ ሌሎች ፋብሪካዎችም የራሳቸውን የግብዓት ሰንሰለት በመዘርጋት የህዝብን የምግብ ዋስትና በዘላቂነት እንዲያረጋግጡ ትልቅ ማበረታቻ ነው ተብሏል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review